የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • መንፈስ ቅዱስ—የእግዚአብሔር አንቀሳቃሽ ኃይል
    በሥላሴ ማመን ይገባሃልን?
    • ማቴዎስ 28:19 ላይ “በመንፈስ ቅዱስ ስም” የሚል አነጋገር ይገኛል። ይሁን እንጂ ስም የሚለው ቃል በግሪክኛም ይሁን በአማርኛ ሁልጊዜ አንድን የተፀውኦ ስም አያመለክትም። “በሕግ ስም” ስንል አንድን የተፀውኦ ስም ያለው አካል ማመልከታችን አይደለም። ሕጉ የቆመለትን ዓላማና ሥልጣን ማመልከታችን ነው። የሮበርትሰን ወርድ ፒክቸር ኢን ዘ ኒው ቴስታመንት (በአዲስ ኪዳን የሚገኝ ሥዕላዊ የቃላት አቀራረብ) እንዲህ ይላል:- “እዚህ ላይ ስም (ኦኖማ) የሚለው ቃል የተሠራበት አጠቃቀም ኃይልንና ሥልጣንን የሚያመለክትና በሴፕቱዋጀንትና በፓፒረስ ጽሑፎች ተዘውትሮ የሚሠራበት አጠቃቀም ነው።” ስለዚህ ‘በመንፈስ ቅዱስ ስም’ መጠመቅ ማለት የመንፈስን ሥልጣን ማወቅና መቀበል እንዲሁም ከእግዚአብሔር የመጣና በመለኮታዊ ፈቃድ የሚንቀሳቀስ መሆኑን መገንዘብ ማለት ነው።

  • ስለ ሥላሴ “ያስረዳሉ” የሚባሉት “ጥቅሶችስ”?
    በሥላሴ ማመን ይገባሃልን?
    • ዘ ኒው ካቶሊክ ኢንሳይክሎፒዲያ ለሥላሴ ማረጋገጫ ይሆናሉ የሚላቸውን ሦስት ጥቅሶች ቢሰጥም የሚከተለውን አምኗል። “የቅዱስ ሥላሴ መሠረተ ትምህርት በብሉይ ኪዳን ውስጥ ፈጽሞ አይገኝም። በአዲስ ኪዳን ውስጥ እጅግ ጥንታዊ ነው የሚባለው ማስረጃ የሚገኘው በጳውሎስ መልእክቶች በተለይ በ​2 ቆሮ 13:13 [በአንዳንድ መጽሐፍ ቅዱሶች በቁጥር 14] እና በ​1 ቆሮ 12:4–6 ላይ ነው። በወንጌሎች ውስጥ ደግሞ የሥላሴ ማስረጃ የምናገኘው በማቴ 28:19 ስለ ጥምቀት በተሰጠው መግለጫ ላይ ነው።”

      በእነዚህ ሦስት ጥቅሶች ላይ ሦስቱ አካላት እንደሚከተለው ተዘርዝረዋል። ሁለተኛ ቆሮንቶስ 13:13 (14) በሚከተለው ሁኔታ ሦስቱን አንድ ላይ አስቀምጧቸዋል። “የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ፣ የእግዚአብሔርም ፍቅር የመንፈስ ቅዱስም ኅብረት ከሁላችሁ ጋር ይሁን።” አንደኛ ቆሮንቶስ 12:4–6 “የጸጋም ስጦታ ልዩ ልዩ ነው፣ መንፈስ ግን አንድ ነው። አገልግሎትም ልዩ ልዩ ነው ጌታም አንድ ነው፤ አሠራርም ልዩ ልዩ ነው፣ ሁሉን በሁሉ የሚያደርግ እግዚአብሔር ግን አንድ ነው።” ማቴዎስ 28:19 ደግሞ እንዲህ ይነበባል:- “እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ፣ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው . . . ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው።”

      ታዲያ እነዚህ ጥቅሶች እግዚአብሔር፣ ክርስቶስና መንፈስ ቅዱስ አንድ ላይ ሆነው አንድ ሥላሴያዊ አምላክ እንደሆኑ ወይም ሦስቱም በሕልውና፣ በኃይልና በዘላለማዊነት እኩል እንደሆኑ ያመለክታሉን? በፍጹም አያመለክቱም። በቀለ፣ አበበና ከበደ አንድ ላይ መጠቀሳቸው ሦስቱ ሰዎች አንድ መሆናቸውን እንደማያመለክት ሁሉ አብ፣ ወልድና መንፈስ ቅዱስ አንድ ላይ መጠቀሳቸውም ሦስቱ አንድ መሆናቸውን ሊያመለክት አይችልም።

      የማክሊንቶክና ስትሮንግ ሳይክሎፒዲያ ኦቭ ቢብሊካል ቴዎሎጂካል ኤንድ ኤክሊዚያስቲካል ሊትሬቸር እንዳመነበት “ሦስቱ አንድ ላይ መዘርዘራቸው የሚያረጋግጠው እነዚህ ሦስት ክፍሎች መኖራቸውን ብቻ ነው። ብቻውን እነዚህ ሦስቱ የመለኮት ክፍል መሆናቸውንና ሦስቱም እኩል የሆነ መለኮታዊ ክብር ያላቸው መሆኑን አያረጋግጥም።”

      ይህ መጽሐፍ የሥላሴ እምነት ደጋፊ ቢሆንም ስለ 2 ቆሮንቶስ 13:13 (14) ሲናገር:- “ከዚህ ጥቅስ እኩል ሥልጣን ወይም አንድ ዓይነት ባሕርይ እንዳላቸው ልንደመድም አንችልም” ብሏል። ስለ ማቴዎስ 28:18–20 ደግሞ እንዲህ ይላል:- “ይህ ጥቅስ ብቻውን የተጠቀሱት ሦስት አካላት ስብዕና እንዳላቸውም ሆነ እኩልነት ወይም መለኮታዊነት እንዳላቸው ሊያረጋግጥ አይችልም።”

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ