-
“ሰብአ ሰገል” እነማን ነበሩ? “ኮከቡን” ያዘጋጀው አምላክ ነው?የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
-
-
“ሰብአ ሰገል” እነማን ነበሩ? “ኮከቡን” ያዘጋጀው አምላክ ነው?
መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?
ብዙዎች ኢየሱስ ሲወለድ “ሰብአ ሰገል” ወይም “ሦስት ጠቢባን” እሱን ለማየት እንደሄዱ ያምናሉ፤ ሆኖም መጽሐፍ ቅዱስ እነዚህን ሰዎች “ሦስቱ ጠቢባን” ወይም “ሦስቱ ነገሥታት” በማለት አይጠራቸውም። (ማቴዎስ 2:1) የወንጌል ጸሐፊ የሆነው ማቴዎስ ኢየሱስን ለማየት የሄዱትን ሰዎች ለመግለጽ ማዪ የሚለውን የግሪክኛ ቃል ተጠቅሟል። ይህ ቃል በኮከብ ቆጠራና በጥንቆላ የተካኑ ሰዎችን የሚያመለክት ሳይሆን አይቀርም።a በመሆኑም አንዳንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞች እነዚህን ሰዎች “ኮከብ ቆጣሪዎች” ወይም “የከዋክብት ተመራማሪዎች” ብለው ይጠሯቸዋል።b
-
-
“ሰብአ ሰገል” እነማን ነበሩ? “ኮከቡን” ያዘጋጀው አምላክ ነው?የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
-
-
“ሰብአ ሰገል” ስንት ነበሩ?
መጽሐፍ ቅዱስ ቁጥራቸው ስንት እንደሆነ አይናገርም፤ እንዲሁም ሰዎች ቁጥራቸውን አስመልክቶ የተለያየ አመለካከት አላቸው። ኢንሳይክሎፒዲያ ብሪታኒካ እንደሚገልጸው ከሆነ “ምሥራቃውያን ሰብአ ሰገል ቁጥራቸው 12 እንደሆነ ያምናሉ፤ ምዕራባውያን ደግሞ ሰብአ ሰገል ሦስት እንደሆኑ ያምናሉ። ምዕራባውያን እንዲህ ያለ አመለካከት የያዙት ሰብአ ሰገል ለሕፃኑ ሦስት ስጦታ ይኸውም ‘ወርቅ፣ ነጭ ዕጣንና ከርቤ’ (ማቴዎስ 2:11) ይዘው በመምጣታቸው ምክንያት ሊሆን ይችላል።”
“ሰብአ ሰገል” ነገሥታት ነበሩ?
ከገና በዓል ጋር በተያያዘ በሚነገሩ ታሪኮች ላይ ሰብአ ሰገል ነገሥታት እንደሆኑ ቢገለጽም መጽሐፍ ቅዱስ እነዚህ ሰዎች ነገሥታት እንደሆኑ አይናገርም። ኢንሳይክሎፒዲያ ብሪታኒካ እንደሚናገረው ከሆነ ኢየሱስ ከተወለደ ከተወሰኑ መቶ ዓመታት በኋላ ሰዎች ስለ ኢየሱስ ልደት በሚገልጸው ታሪክ ላይ አንዳንድ ዝርዝር ነገሮችን በመጨመር ሰብአ ሰገል ነገሥታት እንደሆኑ ይናገሩ ጀመር።
“ሰብአ ሰገል” ስማቸው ማን ነበር?
መጽሐፍ ቅዱስ የኮከብ ቆጣሪዎቹን ስም አይናገርም። ኢንተርናሽናል ስታንዳንርድ ባይብል ኢንሳይክሎፒዲያ እንደሚናገረው “ስማቸው (ለምሳሌ ጋስፓር፣ ሜልክዮርና ባልታዛር) የመጣው ከአፈ ታሪኮች ነው።”
-