-
የክርስቲያኖች ትምህርት ማኅበረሰቡን የሚጠቅመው እንዴት ነው?መጠበቂያ ግንብ—2012 | ግንቦት 1
-
-
ኢየሱስ፣ ሰዎችን ‘ደቀ መዛሙርት እንዲያደርጉ’ ለተከታዮቹ የሰጠውን ትእዛዝ መፈጸም የምድር ጨውና የዓለም ብርሃን እንዲሆኑ የሰጠውን መመሪያ ከመታዘዝ ጋር የተያያዘ ነው። (ማቴዎስ 5:13, 14) እንዴት? ደቀ መዛሙርት የማድረጉ ሥራ በሰዎች ላይ ምን በጎ ተጽዕኖ ያሳድራል?
-
-
የክርስቲያኖች ትምህርት ማኅበረሰቡን የሚጠቅመው እንዴት ነው?መጠበቂያ ግንብ—2012 | ግንቦት 1
-
-
ስለ ብርሃን የሚገልጸውን ዘይቤ በተመለከተስ ምን ማለት ይቻላል? ጨረቃ ከፀሐይ የምታገኘውን ብርሃን እንደምታንጸባርቅ ሁሉ የክርስቶስ ተከታዮችም ከይሖዋ አምላክ የሚመነጨውን “ብርሃን” ያንጸባርቃሉ። ብርሃን በሚፈነጥቀው የሚሰብኩት መልእክትና በሚያከናውኗቸው መልካም ተግባራት አማካኝነት የአምላክን ብርሃን ያንጸባርቃሉ።—1 ጴጥሮስ 2:12
ኢየሱስ ብርሃን በመሆንና ደቀ መዝሙር በመሆን መካከል ያለውን ተመሳሳይነት ጎላ አድርጎ ሲገልጽ እንዲህ ብሏል፦ “ሰዎች መብራት አብርተው እንቅብ አይደፉበትም፤ ከዚህ ይልቅ በመቅረዝ ላይ ያስቀምጡታል፣ በቤት ውስጥ ላሉትም ሁሉ ያበራል። በተመሳሳይም . . . ብርሃናችሁ በሰው ፊት ይብራ።” በመቅረዝ ላይ የተቀመጠ መብራት በአካባቢው ላሉ ሰዎች ሁሉ በግልጽ ይታያል። በተመሳሳይም እውነተኛ ክርስቲያኖች የሚያከናውኑት የስብከት ሥራም ሆነ መልካም ተግባራቸው በአካባቢያቸው ለሚኖሩ ሰዎች በግልጽ ሊታይ ይገባል። ለምን? ክርስቲያኖች የሚያከናውኑትን መልካም ተግባር ያዩ ሰዎች ለእነሱ ሳይሆን ለአምላክ ክብር እንደሚሰጡ ኢየሱስ ተናግሯል።—ማቴዎስ 5:14-16
የጋራ ኃላፊነት
ኢየሱስ “እናንተ የዓለም ብርሃን ናችሁ” እንዲሁም “ብርሃናችሁ በሰው ፊት ይብራ” ብሎ የተናገረው ለሁሉም ደቀ መዛሙርቱ ነበር። በተለያዩ ሃይማኖቶች ውስጥ ተበታትነው የሚገኙ ጥቂት ግለሰቦች ኢየሱስ የሰጠውን ይህን ተልእኮ ሊፈጽሙ አይችሉም። ከዚህ ይልቅ “ብርሃን” የሚሆኑት ሁሉም ተከታዮቹ ናቸው። ከ235 በሚበልጡ አገሮች ውስጥ የሚኖሩ ሰባት ሚሊዮን የይሖዋ ምሥክሮች፣ ክርስቶስ እንዲያውጁ ያዘዛቸውን መልእክት ወደ ሰዎች እየሄዱ የመናገር የጋራ ኃላፊነት እንዳለባቸው ይሰማቸዋል።
-