የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ከሰዎች ጋር ምን ዓይነት ግንኙነት ሊኖረን ይገባል?
    መጠበቂያ ግንብ—2008 | ግንቦት 15
    • 12. (ሀ) ኢየሱስ ስለ መንፈሳዊ ብርሃን ምን ብሏል? (ለ) ብርሃናችንን ማብራት የምንችለው እንዴት ነው?

      12 ሰዎች ከአምላክ የሚገኘውን መንፈሳዊ ብርሃን እንዲያገኙ ስንረዳቸው ከሁሉ የላቀ መልካም ነገር እያደረግንላቸው ነው። (መዝ. 43:3) ኢየሱስ፣ ደቀ መዛሙርቱ “የዓለም ብርሃን” እንደሆኑ የነገራቸው ሲሆን ሰዎች ‘መልካም ሥራቸውን’ ማለትም ለሌሎች የሚያደርጉትን መልካም ነገር ማየት እንዲችሉ ብርሃናቸውን እንዲያበሩ አበረታቷቸዋል። እንዲህ ማድረጋቸው “በሰዎች ፊት” መንፈሳዊ ብርሃን ለማብራት የሚያስችላቸው ሲሆን ይህም ለመላው የሰው ዘር ጥቅም ያስገኛል። (ማቴዎስ 5:14-16⁠ን አንብብ።) በዛሬው ጊዜ ለሌሎች መልካም በማድረግና ምሥራቹን “በዓለም ዙሪያ” ማለትም “ለሕዝብ ሁሉ” በመስበኩ ሥራ በመካፈል ብርሃናችንን ማብራት እንችላለን። (ማቴ. 26:13፤ ማር. 13:10) ይህ እንዴት ያለ ልዩ መብት ነው!

  • ከሰዎች ጋር ምን ዓይነት ግንኙነት ሊኖረን ይገባል?
    መጠበቂያ ግንብ—2008 | ግንቦት 15
    • 14. (ሀ) በመጀመሪያው መቶ ዘመን ኩራዝ የሚሠራው እንዴት ነበር? (ለ) መንፈሳዊውን ብርሃን “ከዕንቅብ ሥር” ማስቀመጥ የለብንም ሲባል ምን ማለት ነው?

      14 ኢየሱስ፣ አንድ ሰው መብራት አብርቶ ከዕንቅብ ሥር እንደማያስቀምጠው ከዚህ ይልቅ ብርሃኑ በቤት ውስጥ ላሉት ሁሉ እንዲያበራ በመቅረዝ ላይ እንደሚያደርገው ተናግሯል። በመጀመሪያው መቶ ዘመን ሰዎች ይጠቀሙበት የነበረው ኩራዝ የሚሠራው ከሸክላ ሲሆን ነዳጅ (አብዛኛውን ጊዜ የወይራ ዘይት) ይጨመርበት ነበር፤ ከዚያም በውስጡ የሚገኘው ክር ጫፉ ሲቀጣጠል ብርሃን ይሰጣል። ይህ ኩራዝ ‘በቤት ውስጥ ላሉት ሁሉ እንዲያበራ’ አብዛኛውን ጊዜ ከእንጨት ወይም ከብረት በተሠራ መቅረዝ ላይ እንጂ ‘ከዕንቅብ ሥር አይቀመጥም’፤ በመጽሐፍ ቅዱስ ዘመን ሰዎች የሚጠቀሙበት ዕንቅብ 9 ኪሎ ያህል የሚይዝ ትልቅ መሥፈሪያ ነበር። ኢየሱስ፣ ደቀ መዛሙርቱ መንፈሳዊ ብርሃናቸውን በምሳሌያዊ ሁኔታ ከዕንቅብ ሥር እንዳያስቀምጡት አሳስቧቸዋል። እኛም፣ ተቃውሞም ሆነ ስደት በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኙትን እውነቶች እንድንደብቅ ወይም ለሌሎች ከመናገር ወደኋላ እንድንል እንዲያደርጉን ባለመፍቀድ ብርሃናችንን ማብራት ይኖርብናል።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ