የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • በአምላክ ፊት ንጹሕ መሆን የምንችለው እንዴት ነው?
    ለዘላለም በደስታ ኑር!—አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ መማሪያ
    • 4. ሱሶችን አስወግድ

      ቆሻሻ መጣያ ውስጥ ሲጋራ እየጣለ ያለ ሰው

      ይሖዋ ማንኛውንም መጥፎ ልማድ እንድናሸንፍ ይረዳናል

      ሲጋራ የምታጨስ ወይም ዕፆችን አላግባብ የምትጠቀም ከሆነ እነዚህን ሱሶች ማሸነፍ ምን ያህል ከባድ እንደሆነ ለመረዳት አትቸገርም። ታዲያ በዚህ ረገድ ምን ሊረዳህ ይችላል? እነዚህ ሱሶች በሕይወትህ ላይ የሚያሳድሩትን ተጽዕኖ ለማሰብ ሞክር። ማቴዎስ 22:37-39⁠ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ ተወያዩ፦

      • አንድ ሰው ሲጋራ ማጨሱ ወይም ዕፆችን አላግባብ መጠቀሙ ከይሖዋ ጋር ያለውን ዝምድና የሚነካበት እንዴት ነው?

      • እንዲህ ማድረጉ በቤተሰቡና በዙሪያው ባሉ ሰዎችስ ላይ ምን ተጽዕኖ ያሳድራል?

      ሱስ ካለብህ፣ ይህን ሱስ ለማስወገድ ዕቅድ አውጣ።b ቪዲዮውን ተመልከቱ።

      ቪዲዮ፦ ራስን የመግዛት ችሎታ ማዳበር (2:47)

      ፊልጵስዩስ 4:13⁠ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተለው ጥያቄ ላይ ተወያዩ፦

      • አንድ ሰው የመጸለይ፣ መጽሐፍ ቅዱስን የማጥናትና በስብሰባዎች ላይ የመገኘት ጥሩ ልማድ ማዳበሩ መጥፎ ልማዶችን ለማሸነፍ ኃይል የሚሰጠው እንዴት ነው?

      5. ንጹሕ ያልሆኑ ሐሳቦችንና ልማዶችን ለማስወገድ ትግል አድርግ

      ቆላስይስ 3:5⁠ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ ተወያዩ፦

      • የብልግና ምስሎችን መመልከት፣ ሴክስቲንግc እንዲሁም ማስተርቤሽን በይሖዋ ዓይን ርኩስ እንደሆኑ ማወቅ የምንችለው እንዴት ነው?

      • ይሖዋ በሥነ ምግባር ንጹሕ እንድንሆን መጠበቁ ምክንያታዊ ይመስልሃል? እንዲህ ብለህ የመለስከው ለምንድን ነው?

      መጥፎ ሐሳቦችን ማስወገድ የሚቻለው እንዴት ነው? ቪዲዮውን ተመልከቱ።

      ቪዲዮ፦ ንጽሕናችሁን ለመጠበቅ ቆራጥ እርምጃ ውሰዱ (1:51)

      ኢየሱስ ሥነ ምግባራዊ ንጽሕናችንን ለመጠበቅ ቆራጥ እርምጃ መውሰድ እንዳለብን የሚያሳይ ምሳሌ ተናግሯል። ማቴዎስ 5:29, 30⁠ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተለው ጥያቄ ላይ ተወያዩ፦

      • ኢየሱስ ቃል በቃል በሰውነታችን ላይ ጉዳት ማድረስ እንዳለብን መናገሩ አልነበረም፤ ከዚህ ይልቅ ቆራጥ እርምጃ መውሰድ እንዳለብን ማመልከቱ ነበር። አንድ ሰው ንጹሕ ያልሆኑ ሐሳቦችን ለማስወገድ ምን ዓይነት ቆራጥ እርምጃ ሊወስድ ይችላል?d

      ንጹሕ ያልሆኑ ሐሳቦችን ለማስወገድ እየታገልክ ከሆነ ይሖዋ የምታደርገውን ጥረት ከፍ አድርጎ ይመለከታል። መዝሙር 103:13, 14⁠ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተለው ጥያቄ ላይ ተወያዩ፦

      • አንድን መጥፎ ልማድ ለማሸነፍ እየታገልክ ከሆነ ይህ ጥቅስ ተስፋ እንዳትቆርጥ የሚረዳህ እንዴት ነው?

      ተስፋ አትቁረጥ!

      አንድ መጥፎ ልማድ ሲያገረሽብህ ‘ምንም ሊሳካልኝ አልቻለም፤ ታዲያ ምን አታገለኝ?’ ብለህ ልታስብ ትችላለህ። ሆኖም ይህን ለማሰብ ሞክር፦ አንድ ሯጭ ተደናቅፎ ወደቀ ማለት በውድድሩ ተሸነፈ ማለት አይደለም፤ ደግሞም ሩጫውን ከመነሻው መጀመር አያስፈልገውም። በተመሳሳይም አንድ መጥፎ ልማድ አገረሸብህ ማለት በምታደርገው ትግል ተሸነፍክ ማለት አይደለም፤ እስከዚያ ጊዜ ድረስ ያደረግከው ጥረትም ከንቱ ይሆናል ማለት አይደለም። አንድን መጥፎ ልማድ ለማሸነፍ በምታደርገው ትግል እንዲህ ያለ ነገር ማጋጠሙ የሚጠበቅ ነው። ስለዚህ ተስፋ አትቁረጥ! በይሖዋ እርዳታ ያለብህን መጥፎ ልማድ ማሸነፍ ትችላለህ።

      ውድድር ውስጥ ያለ ሰው ከወደቀበት ሲነሳ
  • ክርስቲያኖች ለአልኮል መጠጥ ምን አመለካከት ሊኖራቸው ይገባል?
    ለዘላለም በደስታ ኑር!—አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ መማሪያ
    • 6. ከልክ በላይ የመጠጣት ልማድን ማሸነፍ

      ከልክ በላይ ይጠጣ የነበረ አንድ ሰው ይህን ልማድ እንዲያሸንፍ የረዳው ምንድን ነው? ቪዲዮውን ተመልከቱ፤ ከዚያም በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ ተወያዩ፦

      ቪዲዮ፦ ‘በሕይወቴ ተመረርኩ’ (6:32)

      ‘በሕይወቴ ተመረርኩ’ ከሚለው ቪዲዮ ላይ የተወሰዱ ትዕይንቶች፦ 1. ዲሚትሪ የአልኮል መጠጥ የያዘ ጠርሙስ ሲያይ 2. ዲሚትሪ፣ ባለቤቱና ሴት ልጃቸው መጽሐፍ ቅዱስን አብረው ሲያነብቡ
      • በቪዲዮው ላይ ዲሚትሪ የአልኮል መጠጥ ሲጠጣ ምን ዓይነት ጠባይ ያሳይ ነበር?

      • የመጠጥ ሱሱን ወዲያው ማሸነፍ ችሏል?

      • በመጨረሻም ከአልኮል መጠጥ ሱስ መላቀቅ የቻለው እንዴት ነው?

      አንደኛ ቆሮንቶስ 6:10, 11⁠ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ ተወያዩ፦

      • ስካር እንደ ቀላል የሚታይ ጉዳይ ነው?

      • ከልክ በላይ የአልኮል መጠጥ ይጠጣ የነበረ ሰው ሊለወጥ ይችላል የምንለው ለምንድን ነው?

      ማቴዎስ 5:30⁠ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተለው ጥያቄ ላይ ተወያዩ፦

      • ‘እጅን መቁረጥ’ የሚለው አገላለጽ ይሖዋን ለማስደሰት ሲሉ መሥዋዕትነት መክፈልን ያመለክታል። የመጠጥ ሱስን ለማሸነፍ እየታገልክ ከሆነ ምን ማድረግህ ይረዳሃል?a

      አንደኛ ቆሮንቶስ 15:33⁠ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተለው ጥያቄ ላይ ተወያዩ፦

      • ብዙ ከሚጠጡ ሰዎች ጋር ጓደኛ መሆንህ ምን ጉዳት ይኖረዋል?

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ