-
መሣሪያ የታጠቁ ዘራፊዎች ጥቃት ሲሰነዝሩመጠበቂያ ግንብ—1998 | ታኅሣሥ 15
-
-
የታጠቁ ዘራፊዎች ሲመጡ
ይሁንና ዘራፊዎች ቤታችሁ ቢገቡና ቢተናኮሏችሁ ምን ማድረግ አለባችሁ? ሕይወታችሁ ካላችሁ ንብረት ይልቅ ይበልጥ ውድ መሆኑን አስታውሱ። ኢየሱስ ክርስቶስ እንዲህ ብሏል:- “ክፉውን አትቃወሙ፤ ዳሩ ግን ቀኝ ጉንጭህን በጥፊ ለሚመታህ ሁሉ ሁለተኛውን ደግሞ አዙርለት፤ . . . እጀ ጠባብህንም እንዲወስድ ለሚወድ መጎናጸፊያህን ደግሞ ተውለት።”—ማቴዎስ 5:39, 40
ይህ ጥበብ ያለበት ምክር ነው። ክርስቲያኖች ስላላቸው ንብረት ለወንጀለኞች መረጃ የመስጠት ግዴታ ባይኖርባቸውም ዘራፊዎች የተቃውሞና ለመተባበር ፈቃደኛ ያለመሆን መንፈስ ከተመለከቱ ወይም የተታለሉ ሆኖ ከተሰማቸው የኃይል እርምጃ ሊወስዱ ይችላሉ። ብዙዎቹ “የሐፍረት ስሜታቸው ስለጠፋ” በቀላሉ ጨካኞችና ምሕረት የለሾች ሊሆኑ ይችላሉ።—ኤፌሶን 4:19 የ1980 ትርጉም
ሳሙኤል የሚኖረው በአንድ ትልቅ አፓርታማ ውስጥ ነው። ዘራፊዎች የሕንፃውን መተላለፊያዎች በመዝጋት ከአፓርታማ ወደ አፓርታማ እየሄዱ ዘረፉ። ሳሙኤል የተኩስ ድምፅ እንዲሁም በሮች በኃይል ሲዘጉ፣ ሰዎች ሲጮኹና ሲያለቅሱ ይሰማል። አምልጦ መውጣት የማይቻል ነገር ነበር። ሳሙኤል ሚስቱንና ሦስት ወንዶች ልጆቹን በወለሉ ላይ እንዲምበረከኩ፣ እጃቸውን ወደ ላይ እንዲያነሱ፣ ዓይናቸውን እንዲጨፍኑና እንዲጠብቁ ነገራቸው። ዘራፊዎቹ በሩን በርግደው ሲገቡ ሳሙኤል መሬት መሬት እያየ አነጋገራቸው። ይህን ያደረገው ፊታቸውን ካየ ጠቁሞ ሊያስይዘን ይችላል ብለው እንደሚያስቡ ስላወቀ ነበር። “ግቡ” አላቸው። “የፈለጋችሁትን ልትወስዱ ትችላላችሁ። እኛ የይሖዋ ምሥክሮች ነን፤ ምንም አንነካችሁም።” ዘራፊዎቹ በዚህ ነገር ተደነቁ። በሚቀጥለው አንድ ሰዓት ጊዜ ውስጥ በጠቅላላው 12 የሚሆኑ ታጣቂዎች በቡድን በቡድን ሆነው መጡ። ምንም እንኳ ጌጣ ጌጦች፣ ገንዘብና የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ቢዘረፍም ቤተሰቡ በሕንፃው ውስጥ እንደነበሩት እንደሌሎቹ አልተደበደበም ወይም በቆንጨራ የመቆረጥ አደጋ አልደረሰበትም። ሳሙኤልና ቤተሰቡ ሕይወታቸው በመትረፉ ይሖዋን አመስግነዋል።
ይህ እንደሚያሳየው ገንዘብንና ቁሳዊ ነገሮችን በተመለከተ የዝርፊያ ሰለባ የሆኑ ሰዎች ዘራፊዎቹን ከመቃወም መቆጠባቸው የሚደርስባቸውን ጉዳት ሊቀንስ ይችላል።a
-
-
መሣሪያ የታጠቁ ዘራፊዎች ጥቃት ሲሰነዝሩመጠበቂያ ግንብ—1998 | ታኅሣሥ 15
-
-
a የምናሳየው የትብብር መንፈስ ገደብ እንዳለው የተረጋገጠ ነው። የይሖዋ አገልጋዮች የአምላክን ሕግ በሚያስጥስ በማንኛውም መንገድ አይተባበሩም። ለምሳሌ ያህል አንድ ክርስቲያን በፆታ ለመደፈር ፈቃደኛ አይሆንም።
-