የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ኮከብ ቆጣሪዎች ወደ ኢየሱስ መጡ
    ኢየሱስ—መንገድ፣ እውነት፣ ሕይወት
    • የተወሰኑ ሰዎች ከምሥራቅ መጡ። እነዚህ ሰዎች የከዋክብትን አቀማመጥ በማጥናት፣ በሰዎች ሕይወት ውስጥ የሚከሰቱ ነገሮች ያላቸውን ትርጉም እንደሚያውቁ የሚናገሩ ኮከብ ቆጣሪዎች ናቸው። (ኢሳይያስ 47:13) በምሥራቅ በሚገኘው አገራቸው ሳሉ የተመለከቱትን “ኮከብ” ተከትለው በመቶዎች የሚቆጠሩ ኪሎ ሜትሮች ተጉዘዋል፤ “ኮከቡ” የመራቸው ግን ወደ ቤተልሔም ሳይሆን ወደ ኢየሩሳሌም ነው።

      ኮከብ ቆጣሪዎቹ ኢየሩሳሌም ሲደርሱ “የተወለደው የአይሁዳውያን ንጉሥ የሚገኘው የት ነው? በምሥራቅ ሳለን ኮከቡን በማየታችን ልንሰግድለት መጥተናል” በማለት ጠየቁ።—ማቴዎስ 2:1, 2

  • ኮከብ ቆጣሪዎች ወደ ኢየሱስ መጡ
    ኢየሱስ—መንገድ፣ እውነት፣ ሕይወት
    • ኮከብ ቆጣሪዎቹን ሲመራ የነበረውን “ኮከብ” ያዘጋጀው ማን ይመስልሃል? “ኮከቡ” በቤተልሔም ወደነበረው ወደ ኢየሱስ በቀጥታ እንዳልመራቸው አስታውስ። ከዚህ ይልቅ የመራቸው ከንጉሥ ሄሮድስ ጋር ወደተገናኙበት ወደ ኢየሩሳሌም ነው፤ ሄሮድስ ደግሞ ኢየሱስን መግደል ፈለገ። ደግሞም ኢየሱስ የት እንዳለ ኮከብ ቆጣሪዎቹ ለሄሮድስ እንዳይነግሩት አምላክ ጣልቃ ገብቶ ባያስጠነቅቃቸው ኖሮ ሄሮድስ ኢየሱስን ከመግደል አይመለስም። በግልጽ ለመረዳት እንደሚቻለው ኢየሱስ እንዲገደል የፈለገው የአምላክ ጠላት የሆነው ሰይጣን ነው፤ ይህን ዓላማውን ለማሳካትም በዚህ ዘዴ ተጠቅሟል።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ