የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ወደ አምላክ መጸለይ የሚኖርብን እንዴት ነው?
    ንቁ!—2012 | የካቲት
    • ኢየሱስ እንዲህ ብሏል፦ “እንግዲያው እናንተ በዚህ መንገድ ጸልዩ፦ ‘በሰማያት የምትኖር አባታችን፣ ስምህ ይቀደስ። መንግሥትህ ይምጣ። ፈቃድህ በሰማይ እየሆነ እንዳለ ሁሉ በምድርም ላይ ይሁን። የዕለቱን ምግባችንን ዛሬ ስጠን፣ የበደሉንን ይቅር እንዳልን በደላችንን ይቅር በለን። ከክፉው አድነን እንጂ ወደ ፈተና አታግባን።’”​—ማቴዎስ 6:9-13

  • ወደ አምላክ መጸለይ የሚኖርብን እንዴት ነው?
    ንቁ!—2012 | የካቲት
    • “መንግሥትህ ይምጣ።” የአምላክ መንግሥት፣ በሰማይ የሚገኝ መስተዳደር ሲሆን ንጉሡ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ኢየሱስ በቅርቡ መላዋን ምድር ያስተዳድራል። ዳንኤል 7:14 (የ1954 እትም) ለኢየሱስ “ግዛትና ክብር መንግሥትም” እንደተሰጠው ይናገራል። የአምላክ መንግሥት ‘ሲመጣ’ ከሰው ልጆች ጋር በተያያዘ እርምጃ ይወስዳል፤ የእሱ ተቃዋሚ የሆኑ አገዛዞችን በሙሉ ዳግም እንዳያንሰራሩ አድርጎ ከደመሰሰ በኋላ ምድርን ሙሉ በሙሉ ይቆጣጠራል።​—ዳንኤል 2:44

      “ፈቃድህ በሰማይ እየሆነ እንዳለ ሁሉ በምድርም ላይ ይሁን።” በአምላክ መንግሥት አገዛዝ ሥር የሰው ዘር ለአምላክ ፈቃድ ይገዛል። በዚህም የተነሳ እውነተኛ ሰላም የሚሰፍን ሲሆን ሁሉም ሰው ከአምላክ ፈቃድ ጋር በሚስማማ መንገድ እሱን ያመልከዋል። ሰዎችን የሚከፋፍሉ የፖለቲካ ሥርዓቶችም ሆነ የሐሰት ሃይማኖት አይኖሩም። ራእይ 21:3, 4 እንደሚለው በምሳሌያዊ አገላለጽ “የአምላክ ድንኳን ከሰዎች ጋር” ይሆናል፤ አምላክም “እንባን ሁሉ ከዓይኖቻቸው ላይ ይጠርጋል፤ ከእንግዲህ ወዲህ ሞት አይኖርም፤ ሐዘንም ሆነ ጩኸት እንዲሁም ሥቃይ ከእንግዲህ ወዲህ አይኖርም። ቀድሞ የነበሩት ነገሮች አልፈዋል።”

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ