የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w95 9/15 ገጽ 32
  • ከወፎችና ከአበቦች የሚገኝ ትምህርት

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ከወፎችና ከአበቦች የሚገኝ ትምህርት
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1995
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1995
w95 9/15 ገጽ 32

ከወፎችና ከአበቦች የሚገኝ ትምህርት

በአሁኑ ጊዜ ሰዎችን ከሁሉ በላይ የሚያስጨንቃቸው ነገር ምንድን ነው? አብዛኞቹ ለቤተሰቦቻቸው መተዳደሪያ የሚሆን በቂ ገንዘብ የማግኘት ወይም የኑሮ ደረጃቸውን የማሻሻል ጉዳይ ነው።

ኢየሱስ ክርስቶስ ምድር ላይ በነበረበት ጊዜም ቢሆን ለራስና ለቤተሰብ የሚሆን በቂ ገንዘብ የማግኘቱ ጉዳይ አብዛኞቹን ያስጨንቅ ነበር። ይሁን እንጂ እንዲህ ያለው ጤናማ የሆነ ጭንቀት መንፈሳዊ ነገሮችን ሊያጨልም የሚችል ከባድ ጭንቀት ሊሆን ይችላል። ኢየሱስ ይህን ነጥብ በምሳሌ ለማስረዳት ደቀ መዝሙሩን ወፎችንና አበቦችን እንዲመለከቱ ነግሯቸዋል።

ወፎች ምግብን ወደ ኃይል የሚለውጠው በሰውነታቸው ውስጥ ያለው የኬሚካል ሂደት ከፍተኛ በመሆኑ ከሰውነታቸው መጠን አንጻር ሲታይ በየቀኑ ከእኛ የበለጠ መብላት ያስፈልጋቸዋል። ከዚህም በላይ ለወደፊቱ የሚሆናቸውን ዘር መዝራት፣ ማጨድ ወይም ምግብ ማከማቸት አይችሉም። ይሁን እንጂ ኢየሱስ እንደተናገረው ‘የሰማዩ አባታችን ይመግባቸዋል።’ (ማቴዎስ 6:26) በተመሳሳይም አምላክ ውብ የሆኑትን “የሜዳ አበቦች” ባጌጡ ቀለማት አልብሷቸዋል።—ማቴዎስ 6:28–30

ቁሳዊ ፍላጎታችንን በተገቢው ቦታ የምናስቀምጥና ለመንፈሳዊ ነገሮች ቅድሚያ የምንሰጥ ከሆነ አምላክ ለእኛም የሚያስፈልገንን ምግብና ልብስ እንደሚሰጠን ኢየሱስ አረጋግጦልናል። ይሖዋ አምላክ ወፎችንና አበቦችን የሚንከባከብ ከሆነ እርሱን የሚወዱትንና ‘ሳያቋርጡ ጽድቁንና መንግሥቱን የሚያስቀድሙትን’ እንደሚንከባከባቸው የተረጋገጠ ነው። (ማቴዎስ 6:33) የመንግሥቱን ፍላጎቶች በሕይወትህ ውስጥ የመጀመሪያ ቦታ ትሰጣቸዋለህን?

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ