-
መጥምቁ ዮሐንስ መንገዱን አዘጋጀኢየሱስ—መንገድ፣ እውነት፣ ሕይወት
-
-
የዮሐንስ አለባበስም ሆነ ንግግር የሰዎችን ትኩረት የሚስብ ነው። ልብሱ ከግመል ፀጉር የተሠራ ሲሆን ወገቡም ላይ የቆዳ ቀበቶ ይታጠቃል። የሚመገበው ደግሞ አንበጣና የዱር ማር ነው። መልእክቱስ? “መንግሥተ ሰማያት ስለቀረበ ንስሐ ግቡ” የሚል ነው።—ማቴዎስ 3:2
የዮሐንስ መልእክት የአድማጮቹን ስሜት የሚቀሰቅስ ነው። ብዙዎቹ ንስሐ መግባት ማለትም አስተሳሰባቸውንና አካሄዳቸውን በመለወጥ የቀድሞ ሕይወታቸውን እርግፍ አድርገው መተው እንዳለባቸው ተገነዘቡ። “በኢየሩሳሌምና በመላዋ ይሁዳ እንዲሁም በዮርዳኖስ ዙሪያ ባለው ክልል ሁሉ የሚኖሩ ሰዎች” ወደ ዮሐንስ እየመጡ ነው። (ማቴዎስ 3:5) ወደ ዮሐንስ ከመጡት ሰዎች ብዙዎቹ ንስሐ ገብተዋል። እሱም በዮርዳኖስ ወንዝ ውስጥ እያጠለቀ አጠመቃቸው። ይህን ያደረገው ለምንድን ነው?
-
-
መጥምቁ ዮሐንስ መንገዱን አዘጋጀኢየሱስ—መንገድ፣ እውነት፣ ሕይወት
-
-
በእርግጥም ዮሐንስ “መንግሥተ ሰማያት ስለቀረበ ንስሐ ግቡ” ብሎ መናገሩ ተገቢ ነው። (ማቴዎስ 3:2) የዮሐንስ መልእክት፣ ይሖዋ የሾመው ንጉሡ ኢየሱስ ክርስቶስ አገልግሎቱን ሊጀምር መሆኑን ለሕዝቡ የሚጠቁም ነው።
-