የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • “በጣም አዘነላቸው”
    “ተከታዬ ሁን”
    • 15, 16. ኢየሱስ ይሰብክላቸው ለነበሩት ሰዎች ምን አመለካከት እንደነበረው የሚያሳዩ ሁለት ክስተቶች ጥቀስ።

      15 ጊዜው 31 ዓ.ም. ነው፤ ኢየሱስ ለሁለት ዓመት ያህል በቅንዓት ሲያገለግል ቆይቷል፤ አሁን ደግሞ በገሊላ በሚገኙት ‘ከተሞችና መንደሮች እየዞረ’ ይሰብክ ጀመር። በዚያ ያየው ነገር ልቡን በጥልቅ ነካው። ሐዋርያው ማቴዎስ “ሕዝቡንም ባየ ጊዜ እረኛ እንደሌላቸው በጎች ተገፈውና ተጥለው ስለነበር እጅግ አዘነላቸው” በማለት ዘግቧል። (ማቴዎስ 9:​35, 36) ኢየሱስ የሕዝቡ ነገር አንጀቱን በልቶታል። ያሉበትን አሳዛኝ መንፈሳዊ ሁኔታ በሚገባ ተረድቶ ነበር። እንደ እረኛ እነሱን የመጠበቅ ኃላፊነት የነበረባቸው የሃይማኖት መሪዎች በደል እንደሚፈጽሙባቸውና ጨርሶ ቸል እንዳሏቸው ተገንዝቧል። ኢየሱስ ጥልቅ ርኅራኄ ስለገፋፋው ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይል ተስፋ ያዘለውን መልእክት ለሰዎች ሰብኳል። ደግሞም ከአምላክ መንግሥት ምሥራች ይበልጥ የሚያስፈልጋቸው ነገር አልነበረም።

  • “በጣም አዘነላቸው”
    “ተከታዬ ሁን”
    • 18 እኛም ኢየሱስ ለሰዎች የነበረው ዓይነት አመለካከት ሊኖረን ይገባል፤ ኢየሱስ፣ ሕዝቡ “እረኛ እንደሌላቸው በጎች ተገፈውና ተጥለው” እንደነበር ተሰምቶታል። ለምሳሌ አንዲት የባዘነች በግ አገኘህ እንበል። ወደ ግጦሽ ቦታ የሚወስዳትም ሆነ ውኃ የሚያጠጣት እረኛ በማጣቷ በረሃብና በጥም ተጎሳቁላለች። ይህች በግ አታሳዝንህም? የምትበላውና የምትጠጣው ነገር ለመስጠትስ የተቻለህን ጥረት አታደርግም? ምሥራቹን ያልሰሙ ብዙ ሰዎች ከዚህች በግ ጋር በሚመሳሰል ሁኔታ ውስጥ ይገኛሉ። መንፈሳዊ እረኞች ነን የሚሉት የሃይማኖት መሪዎቻቸው ችላ ብለዋቸዋል፤ በዚህም ምክንያት ለመንፈሳዊ ረሃብና ጥማት ከመዳረጋቸውም ሌላ የወደፊቱን ጊዜ በተመለከተ እውነተኛ ተስፋ የላቸውም። እኛ ግን እነሱ የሚያስፈልጋቸው ነገር አለን፤ ይህም በአምላክ ቃል ውስጥ የሚገኘው ገንቢ መንፈሳዊ ምግብና የሚያረካ የእውነት ውኃ ነው። (ኢሳይያስ 55:1, 2) በዙሪያችን ያሉ ሰዎች ያሉበትን መንፈሳዊ እጦት ስናስብ ከልብ እናዝንላቸዋለን። እንደ ኢየሱስ ለሰዎች ከልብ የምናዝን ከሆነ ደግሞ የመንግሥቱን ተስፋ ለእነሱ ለማካፈል የቻልነውን ሁሉ ጥረት እናደርጋለን።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ