የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ስደት ቢኖርም ለመስበክ መዘጋጀት
    ኢየሱስ—መንገድ፣ እውነት፣ ሕይወት
    • ሐዋርያቱ፣ ሁለት ሁለት ሆነው በስብከቱ ሥራ ሲካፈሉ ምን ማድረግ እንዳለባቸው ኢየሱስ ግሩም ሥልጠና ሰጣቸው። ሆኖም ሥልጠናው በዚህ አላበቃም። ተቃዋሚዎች እንደሚያጋጥሟቸው በደግነት ሲያስጠነቅቃቸው እንዲህ አለ፦ “እነሆ፣ በተኩላዎች መካከል እንዳሉ በጎች እልካችኋለሁ፤ . . . ሰዎች ለፍርድ ሸንጎ አሳልፈው ይሰጧችኋል፤ በምኩራቦቻቸውም ይገርፏችኋል፤ ስለዚህ ራሳችሁን ከእነሱ ጠብቁ። ደግሞም በእኔ ምክንያት በገዢዎችና በነገሥታት ፊት ያቀርቧችኋል።”—ማቴዎስ 10:16-18

  • ስደት ቢኖርም ለመስበክ መዘጋጀት
    ኢየሱስ—መንገድ፣ እውነት፣ ሕይወት
    • ኢየሱስ ለ12 ሐዋርያቱ የሰጣቸው መመሪያ፣ ማስጠንቀቂያና ማበረታቻ ምንኛ ጠቃሚ ነው! ኢየሱስ ይህን ሐሳብ የተናገረው እሱ ከሞተና ትንሣኤ ካገኘ በኋላ በስብከቱ ሥራ የሚካፈሉ ሰዎችንም በአእምሮው ይዞ መሆኑን መገንዘብ አያዳግትም። ደቀ መዛሙርቱን የሚጠሏቸው፣ ሐዋርያቱ እንዲሰብኩ በተላኩባቸው ቦታዎች ያሉ ሰዎች ብቻ ሳይሆኑ ‘ሁሉም ሰዎች’ መሆናቸው ይህን ይጠቁማል። በተጨማሪም ሐዋርያት በገሊላ በተካሄደውና ለአጭር ጊዜ በቆየው በዚህ የስብከት ዘመቻ ሲካፈሉ በገዢዎችና በነገሥታት ፊት እንደቀረቡ ወይም የቤተሰባቸው አባላት ለሞት አሳልፈው እንደሰጧቸው የሚገልጽ ዘገባ አናገኝም።

      ኢየሱስ እነዚህን ነገሮች ለደቀ መዛሙርቱ የተናገረው የወደፊቱን ጊዜ በአእምሮው ይዞ እንደሆነ በግልጽ መመልከት ይቻላል። “የሰው ልጅ እስከሚመጣ ድረስ” ደቀ መዛሙርቱ የስብከቱን ሥራ እንደማያጠናቅቁ የተናገረውን ሐሳብ እንመልከት። ይህን ሲል፣ ክብር የተላበሰው ንጉሡ ኢየሱስ ክርስቶስ በአምላክ የተሾመ ፈራጅ ሆኖ ከመምጣቱ በፊት ደቀ መዛሙርቱ ስለ አምላክ መንግሥት የመስበኩን ሥራ እንደማይጨርሱ መናገሩ ነው።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ