-
ኢየሱስ ተጠመቀኢየሱስ—መንገድ፣ እውነት፣ ሕይወት
-
-
ሆኖም ኢየሱስ ሲጠመቅ ሌላም የተፈጸመ ነገር አለ። ቅዱሳን መጻሕፍት ‘ሰማያት እንደተከፈቱለት’ ይገልጻሉ። ይህ ምን ማለት ነው? ኢየሱስ ሲጠመቅ፣ ሰው ከመሆኑ በፊት በሰማይ ያሳለፈውን ሕይወት ማስታወስ እንደቻለ የሚያመለክት ሊሆን ይችላል። በመሆኑም ኢየሱስ፣ ወደ ምድር ከመምጣቱ በፊት አምላክ በሰማይ ያስተማረውን እውነት ጨምሮ የይሖዋ መንፈሳዊ ልጅ ሆኖ ያሳለፈውን ሕይወት ማስታወስ ቻለ።
-
-
ኢየሱስ ፈተናዎችን ከተቋቋመበት መንገድ መማርኢየሱስ—መንገድ፣ እውነት፣ ሕይወት
-
-
ኢየሱስ በዮሐንስ ከተጠመቀ በኋላ ወዲያውኑ የአምላክ መንፈስ ወደ ይሁዳ ምድረ በዳ ወሰደው። ኢየሱስ የሚያስብበት ብዙ ነገር አለ። ሲጠመቅ ‘ሰማያት ተከፍተው’ ነበር። (ማቴዎስ 3:16) ይህም በሰማይ የተማራቸውንና ያደረጋቸውን ነገሮች ማስታወስ እንዲችል አድርጎታል። በእርግጥም ብዙ የሚያሰላስልበት ነገር አለው!
-