-
ስደት ቢኖርም ለመስበክ መዘጋጀትኢየሱስ—መንገድ፣ እውነት፣ ሕይወት
-
-
በእርግጥም የኢየሱስ ተከታዮች ከባድ ስደት ሊደርስባቸው ይችላል፤ ያም ቢሆን የሚከተለውን የሚያረጋጋ ተስፋ ሰጣቸው፦ “አሳልፈው ሲሰጧችሁ እንዴት ወይም ምን ብለን እንመልሳለን? ብላችሁ አትጨነቁ፤ የምትናገሩት ነገር በዚያኑ ሰዓት ይሰጣችኋልና፤ በምትናገሩበት ጊዜ ብቻችሁን አይደላችሁም፤ ይልቁንም በእናንተ የሚናገረው የአባታችሁ መንፈስ ነው።” ኢየሱስ አክሎም እንዲህ አለ፦ “ወንድም ወንድሙን፣ አባትም ልጁን ለሞት አሳልፎ ይሰጣል፤ ልጆችም በወላጆቻቸው ላይ ይነሳሉ፤ ደግሞም ያስገድሏቸዋል። በስሜ የተነሳም ሰዎች ሁሉ ይጠሏችኋል፤ እስከ መጨረሻው የጸና ግን ይድናል።”—ማቴዎስ 10:19-22
-
-
ስደት ቢኖርም ለመስበክ መዘጋጀትኢየሱስ—መንገድ፣ እውነት፣ ሕይወት
-
-
ኢየሱስ ለ12 ሐዋርያቱ የሰጣቸው መመሪያ፣ ማስጠንቀቂያና ማበረታቻ ምንኛ ጠቃሚ ነው! ኢየሱስ ይህን ሐሳብ የተናገረው እሱ ከሞተና ትንሣኤ ካገኘ በኋላ በስብከቱ ሥራ የሚካፈሉ ሰዎችንም በአእምሮው ይዞ መሆኑን መገንዘብ አያዳግትም። ደቀ መዛሙርቱን የሚጠሏቸው፣ ሐዋርያቱ እንዲሰብኩ በተላኩባቸው ቦታዎች ያሉ ሰዎች ብቻ ሳይሆኑ ‘ሁሉም ሰዎች’ መሆናቸው ይህን ይጠቁማል። በተጨማሪም ሐዋርያት በገሊላ በተካሄደውና ለአጭር ጊዜ በቆየው በዚህ የስብከት ዘመቻ ሲካፈሉ በገዢዎችና በነገሥታት ፊት እንደቀረቡ ወይም የቤተሰባቸው አባላት ለሞት አሳልፈው እንደሰጧቸው የሚገልጽ ዘገባ አናገኝም።
ኢየሱስ እነዚህን ነገሮች ለደቀ መዛሙርቱ የተናገረው የወደፊቱን ጊዜ በአእምሮው ይዞ እንደሆነ በግልጽ መመልከት ይቻላል። “የሰው ልጅ እስከሚመጣ ድረስ” ደቀ መዛሙርቱ የስብከቱን ሥራ እንደማያጠናቅቁ የተናገረውን ሐሳብ እንመልከት። ይህን ሲል፣ ክብር የተላበሰው ንጉሡ ኢየሱስ ክርስቶስ በአምላክ የተሾመ ፈራጅ ሆኖ ከመምጣቱ በፊት ደቀ መዛሙርቱ ስለ አምላክ መንግሥት የመስበኩን ሥራ እንደማይጨርሱ መናገሩ ነው።
-