የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • በኢየሱስ ምክንያት ትሰናከላለህ?
    መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2021 | ግንቦት
    • 3 ኢየሱስ አብዛኞቹ ሰዎች የእሱን መሲሕነት እንደማይቀበሉ ያውቅ ነበር። (ዮሐ. 5:39-44) ለመጥምቁ ዮሐንስ ደቀ መዛሙርት “በእኔ ምክንያት የማይሰናከል ደስተኛ ነው” ብሏቸዋል። (ማቴ. 11:2, 3, 6) ይሁንና ብዙ ሰዎች ኢየሱስን ያልተቀበሉት ለምንድን ነው?

  • በኢየሱስ ምክንያት ትሰናከላለህ?
    መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2021 | ግንቦት
    • (1) የኢየሱስ የኋላ ታሪክ

      ናትናኤል ኢየሱስን እንዲተዋወቀው ፊልጶስ ሲያበረታታው፤ ኢየሱስ በአቅራቢያቸው ተቀምጧል።

      ብዙዎች በኢየሱስ የኋላ ታሪክ ተሰናክለዋል። ይኸው ነገር በዛሬው ጊዜ አንዳንዶችን ሊያሰናክል የሚችለው እንዴት ነው? (አንቀጽ 5ን ተመልከት)b

      5. አንዳንዶች ኢየሱስ ተስፋ የተሰጠበት መሲሕ ሊሆን እንደማይችል የተሰማቸው ለምን ሊሆን ይችላል?

      5 ብዙዎች በኢየሱስ እንዲሰናከሉ ያደረጋቸው የኋላ ታሪኩ ነው። ኢየሱስ ግሩም አስተማሪ እንደሆነና ብዙ ተአምራትን እንደሠራ ተቀብለው ነበር። ሆኖም በእነሱ ዓይን ኢየሱስ የአንድ ድሃ አናጺ ልጅ ብቻ ነበር። በዚያ ላይ ደግሞ ኢየሱስ ያደገው በናዝሬት ነው፤ ናዝሬት ያን ያህል ትኩረት የሚሰጣት ከተማ አልነበረችም። ከጊዜ በኋላ የኢየሱስ ደቀ መዝሙር የሆነው ናትናኤል እንኳ “ደግሞ ከናዝሬት ጥሩ ነገር ሊገኝ ይችላል?” ብሏል። (ዮሐ. 1:46) ናትናኤል፣ ኢየሱስ በወቅቱ የሚኖርባትን ከተማ አይወዳት ይሆናል። አሊያም ደግሞ በሚክያስ 5:2 ላይ የሚገኘውን ትንቢት አስታውሶ ሊሆን ይችላል፤ ትንቢቱ እንደሚገልጸው መሲሑ የሚወለደው በናዝሬት ሳይሆን በቤተልሔም ነው።

      6. በኢየሱስ ዘመን የኖሩ ሰዎች እሱ መሲሕ መሆኑን ሊያውቁ ይገባ ነበር የምንለው ለምንድን ነው?

      6 ቅዱሳን መጻሕፍት ምን ይላሉ? ነቢዩ ኢሳይያስ፣ የኢየሱስ ጠላቶች ‘ትኩረት ሰጥተው የመሲሑን ትውልድ በዝርዝር ለማወቅ እንደማይሞክሩ’ ትንቢት ተናግሮ ነበር። (ኢሳ. 53:8) በቅዱሳን መጻሕፍት ውስጥ ስለ መሲሑ በዝርዝር የሚናገሩ በርካታ ትንቢቶች ይገኛሉ። በኢየሱስ ዘመን የነበሩት ሰዎች ጊዜ ወስደው መረጃዎቹን በሙሉ ቢመረምሩ ኖሮ ኢየሱስ የተወለደው በቤተልሔም እንደሆነና የንጉሥ ዳዊት ዘር መሆኑን ይገነዘቡ ነበር። (ሉቃስ 2:4-7) በእርግጥም በሚክያስ 5:2 ላይ ከሚገኘው ትንቢት ጋር በሚስማማ መልኩ ኢየሱስ የተወለደው በቤተልሔም ነው። ታዲያ ችግሩ ምን ነበር? ሰዎቹ ድምዳሜ ላይ ለመድረስ መቸኮላቸው ነው። የተሟላ መረጃ አልነበራቸውም። በዚህም ምክንያት ተሰናከሉ።

  • በኢየሱስ ምክንያት ትሰናከላለህ?
    መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2021 | ግንቦት
    • (2) ኢየሱስ ለታይታ ብሎ ምልክት አላሳየም

      ኢየሱስ ብዙ ሰዎችን ሲያስተምር።

      ብዙዎች ኢየሱስ ለታይታ ብሎ ምልክት ባለማሳየቱ ተሰናክለዋል። ይኸው ነገር በዛሬው ጊዜ አንዳንዶችን ሊያሰናክል የሚችለው እንዴት ነው? (ከአንቀጽ 9-10ን ተመልከት)c

      9. ኢየሱስ ከሰማይ ምልክት ለማሳየት ፈቃደኛ አለመሆኑ ምን አስከትሏል?

      9 በኢየሱስ ዘመን የኖሩ አንዳንድ ሰዎች ግሩም የሆኑ ትምህርቶቹን መስማታቸው ብቻ አላረካቸውም። ተጨማሪ ነገር ፈልገው ነበር። መሲሕ መሆኑን ለማረጋገጥ “ከሰማይ ምልክት እንዲያሳያቸው ጠየቁት።” (ማቴ. 16:1) ምናልባትም ይህን ጥያቄ ያቀረቡት ዳንኤል 7:13, 14⁠ን በተሳሳተ መንገድ ስለተረዱት ሊሆን ይችላል። ሆኖም በይሖዋ የጊዜ ሰሌዳ መሠረት ይህ ትንቢት የሚፈጸምበት ጊዜ ገና አልደረሰም ነበር። ኢየሱስ የሚያስተምረው ነገር እሱ መሲሕ መሆኑን የሚያሳይ በቂ ማስረጃ ሊሆናቸው ይገባ ነበር። ኢየሱስ የጠየቁትን ምልክት ለማሳየት ፈቃደኛ አለመሆኑ እንዲሰናከሉ አደረጋቸው።—ማቴ. 16:4

      10. ኢየሱስ፣ ኢሳይያስ ስለ መሲሑ የጻፈውን ትንቢት የፈጸመው እንዴት ነው?

      10 ቅዱሳን መጻሕፍት ምን ይላሉ? ነቢዩ ኢሳይያስ ስለ መሲሑ ሲጽፍ “አይጮኽም ወይም ድምፁን ከፍ አያደርግም፤ ድምፁንም በጎዳና ላይ አያሰማም” ብሎ ነበር። (ኢሳ. 42:1, 2) ኢየሱስ አገልግሎቱን ያከናወነው ወደ ራሱ ትኩረት በሚስብ መንገድ አልነበረም። ኢየሱስ ግዙፍ የሆኑ ቤተ መቅደሶችን አልገነባም፤ ለየት ያለ ሃይማኖታዊ ልብስ አልለበሰም፤ ወይም ሰዎች በሃይማኖታዊ የማዕረግ ስሞች እንዲጠሩት አልጠየቀም። ሞት ሊፈረድበት በነበረ ጊዜ እንኳ ኢየሱስ ንጉሥ ሄሮድስን የሚያስደምም ተአምር ለመፈጸም ፈቃደኛ አልሆነም። (ሉቃስ 23:8-11) እርግጥ ኢየሱስ ተአምራት የፈጸመባቸው ጊዜያት አሉ፤ ሆኖም በዋነኝነት ትኩረት ያደረገው ምሥራቹን በመስበኩ ላይ ነበር። ደቀ መዛሙርቱን “የመጣሁት ለዚሁ ነው” ብሏቸዋል።—ማር. 1:38

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ