የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • “ይሖዋ አምላክህን ብቻ አምልክ”
    የይሖዋ ንጹሕ አምልኮ መልሶ ተቋቋመ!
    • 1, 2. ኢየሱስ በ29 ዓ.ም. የመከር ወቅት ላይ በይሁዳ ምድረ በዳ ሊገኝ የቻለው እንዴት ነው? በዚያስ ምን አጋጠመው? (በመግቢያው ላይ ያለውን ሥዕል ተመልከት።)

      ጊዜው 29 ዓ.ም. የመከር ወቅት መጀመሪያ ሲሆን ኢየሱስ ከሙት ባሕር በስተ ሰሜን በይሁዳ ምድረ በዳ ይገኛል። ከተጠመቀና ከተቀባ በኋላ ኢየሱስን ወደዚህ ስፍራ የመራው መንፈስ ቅዱስ ነው። ያገጠጡ ድንጋዮችና ገደላ ገደሎች በሞሉበት በዚህ ጠፍ ምድረ በዳ ባሳለፋቸው 40 ቀናት የሚጾምበት፣ የሚጸልይበትና የሚያሰላስልበት አጋጣሚ አግኝቷል። ምናልባትም በዚህ ወቅት ይሖዋ ልጁን በማነጋገር ወደፊት ለሚጠብቀው ነገር አዘጋጅቶት ሊሆን ይችላል።

      2 ኢየሱስ በጣም ከመራቡ የተነሳ ተዳክሞ በነበረበት ወቅት ሰይጣን ወደ እሱ ቀረበ። ቀጥሎ የተከናወነው ነገር አንተን ጨምሮ ንጹሕ አምልኮን የሚወዱ ሰዎችን በሙሉ ከሚነካ አንድ አንገብጋቢ ጉዳይ ጋር በቀጥታ የተያያዘ ነው።

  • “ይሖዋ አምላክህን ብቻ አምልክ”
    የይሖዋ ንጹሕ አምልኮ መልሶ ተቋቋመ!
    • 3, 4. (ሀ) ሰይጣን የመጀመሪያዎቹን ሁለት ፈተናዎች የጀመረው በየትኞቹ ቃላት ነው? ይህን ያለውስ ኢየሱስ ስለ ምን ነገር ጥርጣሬ እንዲያድርበት ለማድረግ ፈልጎ ሊሆን ይችላል? (ለ) በዛሬው ጊዜ ሰይጣን ተመሳሳይ ዘዴዎችን የሚጠቀመው እንዴት ነው?

      3 ማቴዎስ 4:1-7⁠ን አንብብ። ሰይጣን የመጀመሪያዎቹን ሁለት ፈተናዎች ያቀረበው “የአምላክ ልጅ ከሆንክ” የሚሉትን ተንኮል ያዘሉ ቃላት በማስቀደም ነበር። ሰይጣን ይህን ያለው ኢየሱስ የአምላክ ልጅ መሆኑን ተጠራጥሮ ነው? በፍጹም። ከአምላክ ልጆች አንዱ የነበረው ይህ ዓመፀኛ መልአክ ኢየሱስ የአምላክ የበኩር ልጅ መሆኑን ጠንቅቆ ያውቃል። (ቆላ. 1:15) ሰይጣን፣ ኢየሱስ በተጠመቀበት ወቅት ይሖዋ “በጣም የምደሰትበት የምወደው ልጄ ይህ ነው” በማለት ከሰማይ ሲናገር እንደሰማም ምንም ጥርጥር የለውም። (ማቴ. 3:17) ምናልባትም የሰይጣን ዓላማ ኢየሱስ፣ አባቱ እምነት የሚጣልበትና ለእሱ ከልብ የሚያስብ መሆኑን እንዲጠራጠር ማድረግ ሊሆን ይችላል። ዲያብሎስ ለኢየሱስ ባቀረበው የመጀመሪያ ፈተና ላይ “የአምላክ ልጅ ከሆንክ እስቲ እነዚህ ድንጋዮች ዳቦ እንዲሆኑ እዘዝ” ሲል፣ በተዘዋዋሪ መንገድ ‘የአምላክ ልጅ አይደለህ? ታዲያ በዚህ ጠፍ ምድረ በዳ ውስጥ አባትህ የማይመግብህ ለምንድን ነው?’ ማለቱ ነበር። በሁለተኛው ፈተና ላይ ደግሞ ወደ ቤተ መቅደሱ አናት ወስዶ “የአምላክ ልጅ ከሆንክ እስቲ ራስህን ወደ ታች ወርውር” ሲለው ‘እንግዲህ የአምላክ ልጅ ነኝ ብለሃል፤ ታዲያ አባትህ በእርግጥ እንደሚጠብቅህ ትተማመናለህ?’ ያለው ያህል ነበር።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ