የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • የመጽሐፍ ቅዱስ መጽሐፍ ቁጥር 32—ዮናስ
    “ቅዱሳት መጻሕፍት ሁሉ” ትክክለኛና ጠቃሚ ናቸው፣ ጥራዝ 15
    • 3 መላው የዮናስ መጽሐፍ እውነተኛ ታሪክ መሆኑ ምንም አያጠያይቅም። ‘የእምነታችን ፍጹም አድራጊ የሆነው ኢየሱስ’ ዮናስ በእርግጥ የነበረ ሰው መሆኑን ከማመልከቱም ሌላ በዮናስ መጽሐፍ ውስጥ የተገለጹ ሁለት ትንቢታዊ ክንውኖች ያላቸውን ትርጉም ገልጿል። በዚህ መንገድ የዮናስ መጽሐፍ እውነተኛ ትንቢት የያዘ መሆኑን አረጋግጧል። (ዕብ. 12:2፤ ማቴ. 12:39-41፤ 16:4፤ ሉቃስ 11:29-32) አይሁዳውያን ምን ጊዜም ቢሆን የዮናስን መጽሐፍ ከቅዱሳን መጻሕፍት አንዱ እንደሆነ የተቀበሉት ከመሆኑም በላይ እንደ ታሪክ መጽሐፍ አድርገው ይመለከቱታል። ዮናስ የራሱን ስህተቶችና ድክመቶች ሳይሸፋፍን በፍጹም ግልጽነትና በሐቀኝነት መግለጹ መጽሐፉ ትክክለኛ መሆኑን ያረጋግጣል።

  • የመጽሐፍ ቅዱስ መጽሐፍ ቁጥር 32—ዮናስ
    “ቅዱሳት መጻሕፍት ሁሉ” ትክክለኛና ጠቃሚ ናቸው፣ ጥራዝ 15
    • 11 ኢየሱስ በማቴዎስ 12:38-41 ላይ ለሃይማኖት መሪዎች “ከነቢዩ ዮናስ ምልክት በስተቀር” ሌላ ምልክት እንደማይሰጣቸው ነግሯቸዋል። ዮናስ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት ‘በመቃብር ጥልቅ’ ከቆየ በኋላ ወደ ነነዌ ሄዶ በመስበኩ ለነነዌ ሰዎች “ምልክት” ሆኖላቸዋል። (ዮናስ 1:17፤ 2:2፤ 3:1-4) ኢየሱስም በተመሳሳይ ሦስት ቀን ያህል መቃብር ውስጥ ከቆየ በኋላ ተነስቷል። የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት ይህ መፈጸሙን የሚያረጋግጥ ማስረጃ በማቅረብ ሲሰብኩ ኢየሱስ ለዚያ ትውልድ ምልክት ሆኗል። በኢየሱስ ላይ የተፈጸመውን ሁኔታ ከአይሁዳውያን የጊዜ አቆጣጠር ጋር አገናዝበን ስንመለከት ከሦስት ሙሉ ቀናት ያነሰው ይህ ጊዜ “ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት” ሊባል ይችላል።b

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ