የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ሰማያዊ ዜግነት ያላቸው ክርስቲያን ምሥክሮች
    መጠበቂያ ግንብ—1995 | ሐምሌ 1
    • 2. አጥማቂው ዮሐንስ ኢየሱስ ምን አዲስ ነገር እንደሚያደርግ አስታውቆ ነበር? ይህ አዲስ ነገር ከምን ነገር ጋር ግንኙነት ነበረው?

      2 አጥማቂው ዮሐንስ ለኢየሱስ መንገዱን ሲጠርግ ኢየሱስ አንድ አዲስ ነገር እንደሚያደርግ አስታውቋል። ታሪኩ እንዲህ ይላል፦ “[ዮሐንስ] ተጎንብሼ የጫማውን ጠፍር መፍታት የማይገባኝ ከእኔ የሚበረታ በኋላዬ ይመጣል። እኔ በውኃ አጠመቅኋችሁ እርሱ ግን በመንፈስ ቅዱስ ያጠምቃችኋል እያለ ይሰብክ ነበር።” (ማርቆስ 1:7, 8) ከዚያ ጊዜ በፊት ማንም ሰው በመንፈስ ቅዱስ ተጠምቆ አያውቅም። ይህ መንፈስ ቅዱስን የሚመለከት አዲስ ዝግጅት ነበር፤ ይሖዋ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ሰዎችን ለሰማያዊ አገዛዝ ለማዘጋጀት ካለው ዓላማ ጋር ግንኙነት ያለው ነገር ነበር።

  • ሰማያዊ ዜግነት ያላቸው ክርስቲያን ምሥክሮች
    መጠበቂያ ግንብ—1995 | ሐምሌ 1
    • 5. ታማኝ ደቀ መዛሙርት ለመጀመሪያ ጊዜ በመንፈስ ቅዱስ የተጠመቁት መቼ ነበር? በዚሁ ወቅት ከዚህ ጋር ግንኙነት ያላቸው ምን የመንፈስ ቅዱስ አሠራሮች ተከሰቱ?

      5 ኢየሱስ ከኒቆዲሞስ ጋር ከመነጋገሩ በፊት መንፈስ ቅዱስ ወርዶበት በአምላክ መንግሥት ውስጥ ወደፊት ለሚያገኘው ንግሥና ተቀብቶ ነበር፤ በተጨማሪም አምላክ በይፋ እንደ ልጁ አድርጎ እንደተቀበለው አሳውቆ ነበር። (ማቴዎስ 3:16, 17) በ33 እዘአ በጰንጠቆስጤ ዕለት ይሖዋ ተጨማሪ መንፈሳዊ ልጆችን ወልዷል። በኢየሩሳሌም ውስጥ በሚገኝ አንድ ሰገነት ላይ የተሰበሰቡ ታማኝ ደቀ መዛሙርት በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት ተጠመቁ። በዚሁ ወቅት የአምላክ መንፈሳዊ ልጆች እንዲሆኑ ከመንፈስ ቅዱስ ተወለዱ። (ሥራ 2:2–4, 38፤ ሮሜ 8:15) ከዚህም በላይ ወደፊት የአምላክ መንግሥት ወራሾች እንዲሆኑ በመንፈስ ቅዱስ ተቀቡ፤ ለሰማያዊ ተስፋቸው እርግጠኛነት ምልክት እንዲሆንም ለመጀመሪያ ጊዜ በመንፈስ ቅዱስ ታተሙ።—2 ቆሮንቶስ 1:21, 22

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ