-
ከሥራህ እርካታን ማግኘት ትችላለህ‘ከአምላክ ፍቅር አትውጡ’
-
-
6, 7. ኢየሱስ ተግቶ በመሥራት ረገድ ምን የረጅም ጊዜ ታሪክ አስመዝግቧል?
6 ኢየሱስ ትጉ ሠራተኛ በመሆን የረዥም ዘመን ታሪክ አስመዝግቧል። ሰው ሆኖ ከመወለዱ በፊት “በሰማያትና በምድር ያሉ” ነገሮች በሙሉ በተፈጠሩበት ጊዜ የአምላክ “ዋና ባለሙያ [“ሠራተኛ፣” የ1954 ትርጉም]” ሆኖ አገልግሏል። (ምሳሌ 8:22-31፤ ቆላስይስ 1:15-17) ኢየሱስ ምድር በነበረበት ጊዜም ታታሪ ሠራተኛ ነበር። ገና በወጣትነቱ የአናጺነት ሙያ ተምሮ ስለነበር “አናጺው”a ተብሎ ተጠርቷል። (ማርቆስ 6:3) ይህ ሥራ በተለይ የእንጨት መሰንጠቂያዎች፣ በኤሌክትሪክ ኃይል የሚንቀሳቀሱ መሣሪያዎች፣ እንዲሁም የግንባታ ሸቀጣሸቀጦች የሚሸጡባቸው መደብሮች ባልነበሩበት በዚያ ዘመን በጣም አድካሚና የተለያዩ ችሎታዎችን የሚጠይቅ ነበር። ኢየሱስ ለሥራ የሚያስፈልገውን እንጨት ለማግኘት ወደ ጫካ ሄዶ ዛፍ ሲቆርጥና የቆረጠውን እንጨት ወደሚሠራበት ቦታ ተሸክሞ ሲያመጣ ይታይህ። ቤት ለመሥራት የጣሪያውን ማገር ሲያዋቅርና በሮቹን፣ አልፎ ተርፎም የቤት ዕቃዎቹን ሲሠራ በዓይነ ሕሊናህ ለመሳል ሞክር። ኢየሱስ፣ የተዋጣለት ሥራ ለመሥራት መትጋት ከፍተኛ እርካታ እንደሚያስገኝ ከራሱ ተሞክሮ እንደተመለከተ ጥርጥር የለውም።
-
-
ከሥራህ እርካታን ማግኘት ትችላለህ‘ከአምላክ ፍቅር አትውጡ’
-
-
a “አናጺ” ተብሎ የተተረጎመው የግሪክኛ ቃል “ቤቶችን ወይም የቤት ዕቃዎችን ወይም ማንኛውንም የእንጨት ሥራ የሚሠራን ሰው የሚያመለክት ሰፋ ያለ ትርጉም ያለው ስያሜ ነው።”
-