የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • lff ትምህርት 17
  • ኢየሱስ ምን ባሕርያት አሉት?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ኢየሱስ ምን ባሕርያት አሉት?
  • ለዘላለም በደስታ ኑር!—አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ መማሪያ
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ጠለቅ ያለ ጥናት
  • ማጠቃለያ
  • ምርምር አድርግ
  • ኢየሱስ ማን ነው?
    ለዘላለም በደስታ ኑር!—አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ መማሪያ
  • ‘ወልድ አብን ለመግለጥ ፈቃደኛ ነው’
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2012
  • ኢየሱስ ክርስቶስ ማን ነው?
    መጽሐፍ ቅዱስ ምን ያስተምረናል?
  • ኢየሱስ ምድር ላይ ሳለ ምን ነገሮችን አከናውኗል?
    ለዘላለም በደስታ ኑር!—አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ መማሪያ
ለተጨማሪ መረጃ
ለዘላለም በደስታ ኑር!—አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ መማሪያ
lff ትምህርት 17
ምዕራፍ 17. ኢየሱስ እጁን ዘርግቶ አንድን የታመመ ሰው በተአምር ሲፈውስ

ምዕራፍ 17

ኢየሱስ ምን ባሕርያት አሉት?

በወረቀት የሚታተመው
በወረቀት የሚታተመው
በወረቀት የሚታተመው

ኢየሱስ ምድር ላይ ሳለ የተናገራቸውንም ሆነ ያደረጋቸውን ነገሮች ስንመረምር ወደ እሱም ሆነ ወደ አባቱ ወደ ይሖዋ እንድንቀርብ የሚያደርጉ ባሕርያት እንዳሉት እንገነዘባለን። ኢየሱስን እንድንወደው ከሚያደርጉን ባሕርያቱ መካከል አንዳንዶቹ የትኞቹ ናቸው? እኛስ የእሱን ምሳሌ መከተል የምንችለው እንዴት ነው?

1. ኢየሱስ አባቱን የሚመስለው በየትኞቹ መንገዶች ነው?

ኢየሱስ በቢሊዮኖች ለሚቆጠሩ ዓመታት በሰማይ ሲኖር አፍቃሪ የሆነውን አባቱን የማየትና ከእሱ የመማር አጋጣሚ አግኝቷል። በዚህም ምክንያት አስተሳሰቡ፣ ስሜቱና ድርጊቱ ልክ እንደ አባቱ ነው። (ዮሐንስ 5:19⁠ን አንብብ።) እንዲያውም ኢየሱስ የአባቱን ባሕርያት በሚገባ ከማንጸባረቁ የተነሳ “እኔን ያየ ሁሉ አብንም አይቷል” ብሎ ሊናገር ችሏል። (ዮሐንስ 14:9) ስለ ኢየሱስ ባሕርያት እየተማርክ በሄድክ መጠን ይሖዋን የበለጠ እያወቅከው ትሄዳለህ። ለምሳሌ ኢየሱስ ለሰዎች ያሳየው ርኅራኄ ይሖዋ ለአንተ ምን ያህል እንደሚያስብልህ ያሳያል።

2. ኢየሱስ ይሖዋን እንደሚወደው ያሳየው እንዴት ነው?

ኢየሱስ “እኔ አብን እንደምወድ ዓለም እንዲያውቅ አብ ባዘዘኝ መሠረት እየሠራሁ ነው” ብሏል። (ዮሐንስ 14:31) ኢየሱስ ምድር ላይ በነበረበት ወቅት በአስቸጋሪ ጊዜም ጭምር አባቱን በመታዘዝ ለእሱ ያለውን ጥልቅ ፍቅር አሳይቷል። በተጨማሪም ኢየሱስ ስለ አባቱ ማውራትና ሌሎች ከአባቱ ጋር ወዳጅነት እንዲመሠርቱ መርዳት ያስደስተው ነበር።—ዮሐንስ 14:23

3. ኢየሱስ ሰዎችን እንደሚወድ ያሳየው እንዴት ነው?

መጽሐፍ ቅዱስ ኢየሱስ ‘በተለይ በሰው ልጆች እጅግ እንደሚደሰት’ ይናገራል። (ምሳሌ 8:31) ሰዎችን በማበረታታትና ራሱን ሳይቆጥብ በመርዳት ፍቅሩን አሳይቷል። የፈጸማቸው ተአምራት ኃይሉን ብቻ ሳይሆን ርኅራኄውንም ያሳያሉ። (ማርቆስ 1:40-42) ለሰዎች ደግነት አሳይቷል፤ እንዲሁም ያለምንም አድልዎ ሁሉንም በእኩል ዓይን ያይ ነበር። የሚናገረው ነገር እሱን ለሚሰሙ ቅን ልብ ያላቸው ሰዎች ሁሉ መጽናኛና ተስፋ የሚሰጥ ነበር። ኢየሱስ ለሰው ልጆች ሁሉ ፍቅር ስላለው ለእነሱ ሲል ለመሠቃየትና ለመሞት ፈቃደኛ ሆኗል። የእሱን ትምህርቶች ለሚከተሉ ሰዎች ደግሞ የተለየ ፍቅር አለው።—ዮሐንስ 15:13, 14⁠ን አንብብ።

ጠለቅ ያለ ጥናት

ስለ ኢየሱስ ባሕርያት በስፋት እንመለከታለን። በተጨማሪም ልክ እንደ እሱ ፍቅርና ልግስና ማሳየት የምንችለው እንዴት እንደሆነ እንወያያለን።

4. ኢየሱስ አባቱን ይወዳል

ኢየሱስ የተወው ምሳሌ አምላክን እንደምንወደው ማሳየት የምንችለው እንዴት እንደሆነ ይጠቁመናል። ሉቃስ 6:12⁠ን እንዲሁም ዮሐንስ 15:10⁠ን እና 17:26⁠ን አንብቡ። እያንዳንዱን ጥቅስ አንብባችሁ በሚከተለው ጥያቄ ላይ ተወያዩ፦

  • የኢየሱስን ምሳሌ በመከተል ይሖዋን እንደምንወደው ማሳየት የምንችለው እንዴት ነው?

ኢየሱስ ሲጸልይ

ኢየሱስ በሰማይ ያለውን አባቱን ይወደው ነበር፤ እንዲሁም እሱን ለማነጋገር በተደጋጋሚ ወደ እሱ ይጸልይ ነበር

5. ኢየሱስ ችግር ላይ ለወደቁ ሰዎች ያዝናል

ኢየሱስ ከራሱ ፍላጎት ይልቅ ለሌሎች ሰዎች ፍላጎት ቅድሚያ ይሰጥ ነበር። ደክሞት እያለም እንኳ ጊዜውንና ጉልበቱን ሳይቆጥብ ሰዎችን ረድቷል። ማርቆስ 6:30-44⁠ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ ተወያዩ፦

  • በዚህ ጥቅስ ላይ ኢየሱስ ለሌሎች እንደሚያስብ ያሳየባቸው አንዳንድ መንገዶች የትኞቹ ናቸው?—ቁጥር 31, 34, 41 እና 42⁠ን ተመልከት።

  • ኢየሱስ ሰዎቹን ለመርዳት የተነሳሳበት ምክንያት ምንድን ነው?—ቁጥር 34⁠ን ተመልከት።

  • ኢየሱስ የይሖዋን ባሕርያት የሚያንጸባርቅ ከመሆኑ አንጻር እሱ ያደረገው ነገር ስለ ይሖዋ ምን ያስተምርሃል?

  • ልክ እንደ ኢየሱስ ለሰዎች እንደምናስብ ማሳየት የምንችልባቸው አንዳንድ መንገዶች የትኞቹ ናቸው?

ኢየሱስ አምስት ዳቦና ሁለት ዓሣ በተአምር በመለወጥ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን መግቧል። ደቀ መዛሙርቱ ምግቡን ለወንዶች፣ ለሴቶችና ለልጆች አከፋፍለዋል

6. ኢየሱስ ለጋስ ነው

ኢየሱስ ብዙ ገንዘብ ባይኖረውም ለሌሎች በልግስና ይሰጥ ነበር፤ እኛንም ለጋስ እንድንሆን አበረታቶናል። የሐዋርያት ሥራ 20:35⁠ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተለው ጥያቄ ላይ ተወያዩ፦

  • ኢየሱስ በተናገረው መሠረት ደስተኛ ለመሆን ምን ማድረግ አለብን?

ቪዲዮውን ተመልከቱ፤ ከዚያም በሚከተለው ጥያቄ ላይ ተወያዩ፦

ቪዲዮ፦ “መስጠት የበለጠ ደስታ ያስገኛል”—ተቀንጭቦ የተወሰደ (4:00)

  • ብዙ ገንዘብ ባይኖረንም እንኳ ለሌሎች መስጠት የምንችልባቸው አንዳንድ መንገዶች የትኞቹ ናቸው?

ይህን ታውቅ ነበር?

መጽሐፍ ቅዱስ በኢየሱስ ስም ወደ ይሖዋ እንድንጸልይ ያስተምረናል። (ዮሐንስ 16:23, 24⁠ን አንብብ።) በዚህ መንገድ ስንጸልይ ኢየሱስ የይሖዋ ወዳጆች እንድንሆን ለተጫወተው ሚና አድናቆት እንዳለን እናሳያለን።

አንዳንዶች እንዲህ ይላሉ፦ “አምላክ በእኛ ላይ የሚደርሰው መከራ አያሳስበውም።”

  • ኢየሱስ የአባቱን ባሕርያት ያንጸባርቃል፤ ከዚህ አንጻር እሱ ያደረገው ነገር ይሖዋ የእኛ ሁኔታ እንደሚያሳስበው የሚያሳየው እንዴት ነው?

ማጠቃለያ

ኢየሱስ ይሖዋንና ሰዎችን ይወዳል። ኢየሱስ የአባቱን ባሕርይ ስለሚያንጸባርቅ ስለ እሱ እያወቅክ በሄድክ መጠን ይሖዋን ይበልጥ እያወቅከው ትሄዳለህ።

ክለሳ

  • የኢየሱስን ምሳሌ በመከተል ይሖዋን እንደምንወደው ማሳየት የምንችለው እንዴት ነው?

  • የኢየሱስን ምሳሌ በመከተል ሰዎችን እንደምንወድ ማሳየት የምንችለው እንዴት ነው?

  • ከኢየሱስ ባሕርያት መካከል አንተን ይበልጥ የሚማርክህ የትኛው ነው?

ግብ

ምርምር አድርግ

ኢየሱስን ለመምሰል የሚያስችሉንን አንዳንድ ባሕርያት ተመልከት።

“ኢየሱስን ለመምሰል የሚያስችሉ ባሕርያት” (ኢየሱስ—መንገድ፣ እውነት፣ ሕይወት ገጽ 317)

በኢየሱስ ስም መጸለይ አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው?

“በኢየሱስ ስም መጸለይ ያለብን ለምንድን ነው?” (መጠበቂያ ግንብ የካቲት 1, 2008)

መጽሐፍ ቅዱስ ኢየሱስ ምን ይመስል እንደነበር የሚጠቁም ፍንጭ ይሰጣል?

“ኢየሱስ ምን ይመስል ነበር?” (ድረ ገጻችን ላይ የወጣ ርዕስ)

ኢየሱስ ለሴቶች ካሳየው ደግነት ምን ትምህርት እናገኛለን?

“አምላክ ሴቶችን በአክብሮትና በአሳቢነት ይይዛቸዋል” (መጠበቂያ ግንብ መስከረም 1, 2012)

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ