የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ‘ክርስቶስ የአምላክ ኃይል ነው’
    ወደ ይሖዋ ቅረብ
    • 18-20. (ሀ) ኢየሱስ ኃይሉን በአግባቡ እንዲጠቀምበት ያነሳሳው ምንድን ነው? (ለ) ኢየሱስ አንድን መስማት የተሳነው ሰው ስለፈወሰበት መንገድ ስታስብ ምን ይሰማሃል?

      18 ኃያል የሆነው ኢየሱስ ሥልጣናቸውን ለሰዎች ችግርና ሥቃይ ደንታ ቢስ በሆነ መንገድ ከሚጠቀሙ ሰብዓዊ ገዢዎች ፈጽሞ የተለየ ነው። ኢየሱስ ለሰዎች ያስባል። የተለያየ መከራና ሥቃይ የሚደርስባቸውን ሰዎች ሲያይ አንጀቱ ስለሚንሰፈሰፍ ችግራቸውን ያስወግድላቸው ነበር። (ማቴዎስ 14:14) ለስሜታቸውና ለፍላጎታቸው ስለሚጨነቅ ኃይሉን በአሳቢነት ይጠቀምበት ነበር። በማርቆስ 7:31-37 ላይ ተጠቅሶ የሚገኘው ልብ የሚነካ ታሪክ ለዚህ ግሩም ምሳሌ ነው።

      19 በዚህ ወቅት ኢየሱስ ሕዝቡ ወደ እሱ ይዘዋቸው የመጡትን በርካታ ሕሙማን ፈውሷል። (ማቴዎስ 15:29, 30) ይሁን እንጂ ኢየሱስ ለአንድ ሰው ልዩ አሳቢነት በማሳየት ለብቻው ነጥሎ ወሰደው። ሰውየው መስማት የተሳነውና የመናገር እክል ያለበት ነበር። ኢየሱስ ይህ ሰው እንደተደናገጠ ወይም እንደተሸማቀቀ አስተውሎ ሊሆን ይችላል። በመሆኑም በአሳቢነት ከሕዝቡ ነጥሎ ገለል ወዳለ ቦታ ወሰደው። ከዚያም ምን ሊያደርግ እንዳሰበ ሰውየው እንዲገነዘብ ለማድረግ ሲል አንዳንድ ምልክቶች ተጠቀመ። “ጣቶቹን በሰውየው ጆሮዎች ውስጥ አስገባ፤ እንትፍ ካለ በኋላም የሰውየውን ምላስ ዳሰሰ።”c (ማርቆስ 7:33) በመቀጠል ኢየሱስ ወደ ሰማይ አሻቅቦ ተመለከተና በረጅሙ ተነፈሰ። ይህን ያደረገው ሰውየው የሚፈወሰው በአምላክ ኃይል መሆኑን እንዲገነዘብ ለማድረግ ነው። በመጨረሻም ኢየሱስ “ተከፈት” አለ። (ማርቆስ 7:34) በዚህ ጊዜ ሰውየው መስማትና አጥርቶ መናገር ቻለ።

  • ‘ክርስቶስ የአምላክ ኃይል ነው’
    ወደ ይሖዋ ቅረብ
    • c እንትፍ ማለት በአይሁዶችም ሆነ በአሕዛብ ዘንድ የተለመደ የፈውስ ምልክት ነበር። ምራቅን ለፈውስ ይጠቀሙበት እንደነበር የሚገልጽ ዘገባ በረቢዎች ጽሑፍ ውስጥ ተጠቅሶ እናገኛለን። ኢየሱስ እንትፍ ያለው ሰውየው ሊፈወስ መሆኑን እንዲገነዘብ ለማድረግ ሊሆን ይችላል። ያም ሆነ ይህ ኢየሱስ ምራቁን ለመፈወስ እንደሚያገለግል መድኃኒት አድርጎ አልተጠቀመበትም።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ