የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 5/06 ገጽ 1
  • ያለማቋረጥ “ይከተለኝ”

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ያለማቋረጥ “ይከተለኝ”
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2006
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የራስን ጥቅም የመሠዋት መንፈስ ማሳየት አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2000
  • ከእንግዲህ ለራሳችን አንኖርም
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2005
  • ሌሎችን በማገልገል የኢየሱስን ምሳሌ ተከተሉ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2022
  • ያለማቋረጥ ኢየሱስን ተከተሉ
    የመንግሥት አገልግሎታችን—1997
ለተጨማሪ መረጃ
የመንግሥት አገልግሎታችን—2006
km 5/06 ገጽ 1

ያለማቋረጥ “ይከተለኝ”

1 በርካታ ሰዎች በሕይወታቸው ውስጥ ትልቁን ቦታ የሚሰጡት ራሳቸውን ለማስደሰት ቢሆንም አብዛኛውን ጊዜ ደስተኞች አይደሉም። በአንጻሩ ግን ኢየሱስ ከራስ ወዳድነት ነጻ በሆነ ስሜት መስጠት እውነተኛ ደስታ እንደሚያመጣ ገልጿል። (ሥራ 20:35) “ሊከተለኝ የሚወድ ቢኖር ራሱን ይካድ፤ . . . ይከተለኝ” በማለት ተናግሯል። (ማር. 8:34) ራስን መካድ አልፎ አልፎ አንዳንድ አስደሳች ነገሮችን የመተው ጉዳይ ብቻ አይደለም። ከዚህ ይልቅ በእያንዳንዱ ቀን ራሳችንን ሳይሆን ይሖዋን ለማስደሰት መጣር ማለት ነው።—ሮሜ 14:8፤ 15:3

2 የሐዋርያው ጳውሎስን ምሳሌ እንመልከት። ጳውሎስ ‘ወደር የሌለውን ክርስቶስ ኢየሱስን ለማወቅ’ ሲል የራሱን ፍላጎት ከማሟላት ይልቅ ከአምላክ መንግሥት ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን አስቀድሟል። (ፊልጵ. 3:7, 8) ሌሎችን ለማገልገል “ያለኝን ሁሉ ራሴንም ጭምር ብሰጥ ደስ ይለኛል” በማለት ተናግሯል። (2 ቆሮ. 12:15) እያንዳንዳችን ራሳችንን እንዲህ እያልን መጠየቅ ይኖርብናል:- ‘ጊዜዬን፣ ጉልበቴን፣ ችሎታዬንና ሀብቴን የምጠቀምበት እንዴት ነው? የምሯሯጠው የራሴን ፍላጎት ለማሟላት ነው ወይስ ይሖዋን ለማስደሰት ጥረት እያደረግሁ ነው?’

3 ለመስጠት የሚያስችሉ አጋጣሚዎች:- የአምላክ ሕዝቦች ሕይወት አድን በሆነው በመንግሥቱ የስብከት ሥራ በየዓመቱ ከአንድ ቢሊዮን በላይ ሰዓት ያሳልፋሉ። በየጉባኤዎቹ ውስጥ የሚገኙ ወጣቶችና አረጋውያን ሌሎችን የሚጠቅሙ የተለያዩ ሥራዎችን ያከናውናሉ። አንዳንዶች የመንግሥቱ ሰባኪዎች ይበልጥ ወደሚያስፈልጉበት ቦታ ይሄዳሉ። ከወረዳ፣ ከልዩና ከአውራጃ ስብሰባዎች እንዲሁም እውነተኛውን አምልኮ ለማስፋፋት የምንጠቀምባቸውን አዳራሾች ከመገንባትም ሆነ ከመጠገን ጋር በተያያዘ መከናወን ያለበት ብዙ ሥራ አለ። ከዚህም በላይ በሆስፒታል አገናኝ ኮሚቴዎች ወይም በሕሙማን ጠያቂ ቡድኖች ውስጥ ያሉ ወንድሞች የሚያደርጉትን ፍቅራዊ እርዳታ አስብ። እንደዚህ ያለው የራስን ጥቅም መሥዋዕት የማድረግ መንፈስ ለዓለም አቀፉ የክርስቲያን ወንድማማች ኅብረት በረከት ነው።—መዝ. 110:3

4 ድንገተኛ አደጋ በሚከሰትበት ጊዜ በተለያየ መልኩ እርዳታ መስጠት የምንችልባቸው አጋጣሚዎች ይፈጠራሉ። ይሁንና አብዛኛውን ጊዜ፣ ማበረታቻ ወይም እርዳታ የሚያስፈልጋቸው የእምነት አጋሮቻችን እንዳሉ ልናስተውል እንችላለን። (ምሳሌ 17:17) ሌሎችን ለማገልገልና የመንግሥቱን ጉዳዮች ለማስቀደም ራሳችንን በፈቃደኝነት ስናቀርብ የኢየሱስን ምሳሌ እየተከተልን ነው። (ፊልጵ. 2:5-8) እንግዲያው ያለማቋረጥ እንዲህ ለማድረግ እንትጋ።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ