-
‘እጅግ ብዙ ሰዎች ወደ እሱ መጡ’“ተከታዬ ሁን”
-
-
2 ኢየሱስ ከአንዳንድ የሃይማኖት መሪዎች ጋር ከበድ ባሉ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ መጨረሱ ነው፤ በኋላ ላይ የሆነ ግርግር ተፈጠረ። ሰዎች ልጆቻቸውን ወደ ኢየሱስ ማምጣት ጀመሩ። ልጆቹ በተለያየ የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ እንደሆኑ ከሁኔታው መረዳት ይቻላል፤ ምክንያቱም ማርቆስ እነሱን ለማመልከት የተጠቀመው፣ ቀደም ሲል የ12 ዓመቷን ልጅ ለመግለጽ የተጠቀመበትን ቃል ሲሆን ሉቃስ ደግሞ የተጠቀመው “ሕፃናት” ተብሎ የተተረጎመውን ቃል ነው። (ሉቃስ 18:15፤ ማርቆስ 5:41, 42፤ 10:13) መቼም ልጆች ባሉበት ጫጫታና ግርግር አይጠፋም። ደቀ መዛሙርቱ ኢየሱስ ሥራ ስለሚበዛበት ለልጆች የሚሆን ጊዜ አይኖረውም ብለው በማሰብ ሳይሆን አይቀርም የልጆቹን ወላጆች ገሠጿቸው። ታዲያ ኢየሱስ ምን አደረገ?
-
-
‘እጅግ ብዙ ሰዎች ወደ እሱ መጡ’“ተከታዬ ሁን”
-
-
4, 5. (ሀ) ኢየሱስ በቀላሉ የሚቀረብ ሰው እንደነበር በምን እርግጠኞች መሆን እንችላለን? (ለ) በዚህ ምዕራፍ ውስጥ የትኞቹን ጥያቄዎች እንመረምራለን?
4 ኢየሱስ ፊቱ የማይፈታ፣ ሰው የማያቀርብ ወይም ኩሩ ቢሆን ኖሮ እነዚህ ልጆች ወደ እሱ እንደማይቀርቡ የታወቀ ነው፤ ወላጆቻቸውም ቢሆኑ በነፃነት ወደ እሱ አይመጡም ነበር። እስቲ ሁኔታውን በዓይነ ሕሊናህ ለመሳል ሞክር፤ ይህ ደግ ሰው ልጆቻቸውን በፍቅር ሲያቀርባቸውና ሲባርካቸው ወላጆቹ ምንኛ ተደስተው ይሆን? ልጆች በአምላክ ፊት ትልቅ ቦታ እንዳላቸው ሲገልጽ ሲሰሙ ፊታቸው በደስታ ፈክቶ መሆን አለበት። አዎ፣ ኢየሱስ ከምንም ነገር በላይ የሚያስጨንቅ ከባድ ኃላፊነት ተሸክሞ ባለበት በዚህ ወቅትም በቀላሉ የሚቀረብ ሰው መሆኑን አሳይቷል።
-