-
ራስህን ለይሖዋ መወሰንና መጠመቅ ያለብህ ለምንድን ነው?ለዘላለም በደስታ ኑር!—አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ መማሪያ
-
-
2. ይሖዋ የተጠመቁ አገልጋዮቹን የሚባርካቸው እንዴት ነው?
ስትጠመቅ፣ ደስተኛ የሆነው የይሖዋ ቤተሰብ አባል ትሆናለህ። የይሖዋን ፍቅር በብዙ መንገዶች የምታይበትና ከአሁኑ የበለጠ ወደ እሱ የምትቀርብበት አጋጣሚ ታገኛለህ። (ሚልክያስ 3:16-18ን አንብብ።) ይሖዋ አባት ይሆንልሃል፤ በተጨማሪም በዓለም ዙሪያ የሚኖሩ አንተንም ሆነ ይሖዋን የሚወዱ መንፈሳዊ ወንድሞችና እህቶች ይኖሩሃል። (ማርቆስ 10:29, 30ን አንብብ።) እርግጥ ነው፣ ከመጠመቅህ በፊት አንዳንድ እርምጃዎችን መውሰድ ያስፈልግሃል። ስለ ይሖዋ መማር፣ እሱን መውደድና በልጁ ላይ እምነት ማሳደር አለብህ። በመጨረሻም ራስህን ለይሖዋ መወሰን ይኖርብሃል። እነዚህን እርምጃዎች በመውሰድ መጠመቅህ ለዘላለም በደስታ መኖር የምትችልበትን አጋጣሚ ይከፍትልሃል። የአምላክ ቃል “ጥምቀት . . . እያዳናችሁ ነው” ይላል።—1 ጴጥሮስ 3:21
-
-
ስደትን በጽናት መቋቋም ትችላለህለዘላለም በደስታ ኑር!—አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ መማሪያ
-
-
ኢየሱስ በግልጽ እንደተናገረው ቤተሰባችን ይሖዋን ለማገልገል ያደረግነውን ውሳኔ ሊቃወም ይችላል። ማቴዎስ 10:34-36ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተለው ጥያቄ ላይ ተወያዩ፦
አንድ ሰው ይሖዋን ለማገልገል ሲወስን ከቤተሰቡ ምን ሊያጋጥመው ይችላል?
ምሳሌ ለማየት ቪዲዮውን ተመልከቱ፤ ከዚያም በሚከተለው ጥያቄ ላይ ተወያዩ፦
የቤተሰብህ አባል ወይም ጓደኛህ ይሖዋን ለማገልገል ያደረግከውን ውሳኔ ቢቃወም ምን ታደርጋለህ?
መዝሙር 27:10ን እና ማርቆስ 10:29, 30ን አንብቡ፤ እያንዳንዱን ጥቅስ ካነበባችሁ በኋላ በሚከተለው ጥያቄ ላይ ተወያዩ፦
በዚህ ጥቅስ ላይ የሚገኘው ሐሳብ ከቤተሰቦችህ ወይም ከጓደኞችህ ተቃውሞ ሲያጋጥምህ የሚረዳህ እንዴት ነው?
-