የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ይህን ያውቁ ኖሯል?
    መጠበቂያ ግንብ—2008 | መጋቢት 1
    • የመበለቲቷ ሁለት ሳንቲሞች ምን ያህል ዋጋ ነበራቸው?

      በመጀመሪያው መቶ ዘመን ከክርስቶስ ልደት በኋላ አይሁዳውያን ለቤተ መቅደሱ የሚከፍሉት ዓመታዊ ግብር ‘ሁለት ዲናር’ ሲሆን ይህም ለሁለት ቀን ሥራ ከሚከፈል ደሞዝ ጋር የሚመጣጠን ነበር። (ማቴዎስ 17:24) ኢየሱስ በአንድ ወቅት፣ ሁለት ድንቢጦች ለ45 ደቂቃ ሥራ ከሚከፈል ደሞዝ ጋር ተመጣጣኝ በሆነ “በአንድ ሳንቲም” ይሸጡ እንደነበር ተናግሯል። እንዲያውም በሁለት ሳንቲሞች ማለትም ለ90 ደቂቃ ሥራ በሚከፈል ደሞዝ አምስት ድንቢጦች ማግኘት ይቻል ነበር።—ማቴዎስ 10:29፤ ሉቃስ 12:6 NW

      ኢየሱስ፣ ድሃዋ መበለት ለቤተ መቅደሱ ስትሰጥ የተመለከተው መዋጮ አምስት ድንቢጥ ከሚገዛበት ዋጋ በጣም ያነሰ ነበር። እነዚህ ሁለት ሳንቲሞች ወይም ሁለት ሌፕተኖች በወቅቱ በእስራኤል ውስጥ ጥቅም ላይ ይውሉ የነበሩ ከመዳብ የተሠሩ የመጨረሻዎቹ ትንሽ ሳንቲሞች ነበሩ። እነዚህ ሁለት ሳንቲሞች ከአንድ ቀን ደሞዝ 1/64ኛ ጋር ተመጣጣኝ ናቸው፤ በሌላ አነጋገር አንድ ሰው በቀን በአማካይ 12 ሰዓት ቢሠራ ለ12 ደቂቃ ሥራ ከሚከፈል ደሞዝ ያነሰ ዋጋ አላቸው።

      ኢየሱስ ክርስቶስ የመበለቲቱን ስጦታ “ከትርፋቸው” ከጣሉት ከሌሎቹ የበለጠ ግምት ሰጥቶታል። ለምን? ዘገባው መበለቲቱ ‘ሁለት ትናንሽ ሳንቲሞች’ እንደነበሯት ይገልጻል፤ በመሆኑም አንዱን ሳንቲም በመስጠት ሌላውን ለራሷ ማስቀረት ትችል ነበር። ሆኖም “ያላትን ሁሉ አውጥታ ለመኖሪያ የሚሆናትን እንዳለ ሰጠች።”—ማርቆስ 12:41-44፤ ሉቃስ 21:2-4

  • ይህን ያውቁ ኖሯል?
    መጠበቂያ ግንብ—2008 | መጋቢት 1
    • [በገጽ 12 ላይ የሚገኝ ሥዕል]

      የሌፕተንን ትክክለኛ መጠን የሚያሳይ ፎቶ

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ