የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • “አንባቢው ያስተውል”
    መጠበቂያ ግንብ—1999 | ግንቦት 1
    • 18, 19. ‘ወደ ተራራዎች መሸሽ’ ማለት ሃይማኖትን መቀየር ማለት እንዳልሆነ ለማሳየት ምን ምክንያቶች ተሰጥተዋል?

      18 ኢየሱስ ‘ርኩሰቱ በተቀደሰው ስፍራ ላይ ስለ መቆሙ’ ከተናገረ በኋላ አስተዋይ ሰዎች እርምጃ እንዲወስዱ አሳስቧል። ኢየሱስ ‘ርኩሰቱ በተቀደሰው ስፍራ በሚቆምበት’ በዚያ የመጨረሻ ሰዓት ላይ ብዙዎች ከሐሰት ሃይማኖት ሸሽተው ወደ እውነተኛው አምልኮ ይመጣሉ ማለቱ ነበርን? በፍጹም። የመጀመሪያ ፍጻሜውን ተመልከት። ኢየሱስ እንዲህ ብሏል:- “በይሁዳ ያሉ ወደ ተራሮች ይሽሹ፣ በሰገነትም ያለ ወደ ቤት አይውረድ ከቤቱም አንዳች ይወስድ ዘንድ አይግባ፣ በእርሻም ያለ ልብሱን ይወስድ ዘንድ ወደ ኋላው አይመለስ። በዚያን ወራትም ለርጉዞችና ለሚያጠቡ ወዮላቸው። ነገር ግን ሽሽታችሁ በክረምት እንዳይሆን ጸልዩ።”​—⁠ማርቆስ 13:​14-18 በሰያፍ የጻፍነው እኛ ነን።

  • “አንባቢው ያስተውል”
    መጠበቂያ ግንብ—1999 | ግንቦት 1
    • 22. ኢየሱስ ወደ ተራራዎች እንድንሸሽ የሰጠውን ምክር ተግባራዊ ማድረጋችን ምንን የሚጨምር ሊሆን ይችላል?

      22 በአሁኑ ጊዜ ታላቁን መከራ የሚመለከት ሙሉ ማብራሪያ ሊኖረን ባይችልም ኢየሱስ የተናገረለት ሽሽት በእኛ ሁኔታ ከአንድ አካባቢ ለቆ ወደ ሌላ አካባቢ መሄድን አያመለክትም ወደሚል መደምደሚያ ብንደርስ ምክንያታዊ ነው። የአምላክ ሕዝቦች በዓለም ዙሪያና በማንኛውም ቦታ ይገኛሉ። መሸሽ አስፈላጊ በሚሆንበት ጊዜ ግን ክርስቲያኖች በእነሱና በሐሰት ሃይማኖታዊ ድርጅቶች መካከል ግልጽ የሆነ ልዩነት መኖሩን በሚያሳይ መንገድ በመመላለስ መቀጠል እንደሚገባቸው እርግጠኞች ልንሆን እንችላለን። በተጨማሪም አንድ ሰው ልብሱን ወይም ሌሎች እቃዎቹን ለመሰብሰብ ወደ ቤቱ ተመልሶ እንዳይሄድ ኢየሱስ የሰጠው ማስጠንቀቂያም ትኩረት የሚያሻው ነው። (ማቴዎስ 24:​17, 18) ስለዚህ ለቁሳዊ ነገሮች ባለን አመለካከት ረገድ ወደፊት የሚመጡ ፈተናዎች ሊኖሩ ይችላሉ፤ በጣም አስፈላጊ የሆኑት ያሉን ቁሳዊ ነገሮች ናቸው ወይስ ይበልጥ አንገብጋቢ የሆነው በአምላክ ጎን ለቆሙ ሰዎች የሚመጣው መዳን ነው? አዎን፣ ሽሽታችን አንዳንድ ችግሮችን ወይም እጦትን የሚጨምር ሊሆን ይችላል። ከይሁዳ ተነሥተው የዮርዳኖስን ወንዝ በማቋረጥ ወደ ፍርግያ እንደ ሸሹት እንደ መጀመሪያው መቶ ዘመን ክርስቲያኖች አስፈላጊ የሆነውን ነገር ሁሉ ለማድረግ ዝግጁዎች መሆን አለብን።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ