የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፍቻ
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
      • ናርዶስ።

        ከናርዶስ ተክል (ናርዶስታኪስ ጃታማንሲ) የሚገኝ እጅግ ውድ የሆነና ጥሩ መዓዛ ያለው ቅባት ሲሆን ፈዘዝ ያለ ቀይ ቀለም አለው። የናርዶስ ዘይት እጅግ ውድ ስለነበር ሰዎች ርካሽ ከሆኑ ዘይቶች ጋር ይቀላቅሉት እንዲሁም አስመስለው ይሠሩት ነበር። ማርቆስና ዮሐንስ፣ በኢየሱስ ላይ የፈሰሰው ዘይት “ንጹሕ ናርዶስ” እንደሆነ የገለጹት ለዚህ ሊሆን ይችላል።–ማር 14:3፤ ዮሐ 12:3

  • የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፍቻ
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
      • አልባስጥሮስ።

        ትንሽ ለሆነ የሽቶ መያዣ ብልቃጥ የተሰጠ ስያሜ ሲሆን እንዲህ ዓይነቱ ብልቃጥ ቀደም ሲል ግብፅ ውስጥ አልባስጥሮን በሚባል ቦታ አቅራቢያ ከሚገኝ ድንጋይ ይሠራ ነበር። ይህ ብልቃጥ አብዛኛውን ጊዜ ቀጭን አንገት እንዲኖረው ተደርጎ የሚሠራ ከመሆኑም ሌላ ይታሸግ ነበር፤ ይህም ውድ የሆነው ሽቶ በኖ እንዳያልቅ ለማድረግ ይረዳል። በኋላም ብልቃጡን ለመሥራት የሚያገለግለው ድንጋይ በዚሁ ስያሜ መጠራት ጀመረ።–ማር 14:3

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ