የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • የአርማትያሱ ዮሴፍ ከእውነት ጎን ቆመ
    መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2017 | ጥቅምት
    • የአርማትያሱ ዮሴፍ በሮማዊው ገዥ ፊት ለመቅረብ እንዴት ድፍረት እንዳገኘ ለራሱም እንግዳ ሆኖበታል። ጳንጥዮስ ጲላጦስ በግትርነቱ የሚታወቅ ሰው ነበር። ሆኖም ኢየሱስ ክብር ባለው መንገድ እንዲቀበር ከተፈለገ አንድ ሰው የግድ ጲላጦስ ፊት ቀርቦ የኢየሱስ አስከሬን እንዲሰጠው መጠየቅ ነበረበት። ዮሴፍ፣ ጲላጦስን ፊት ለፊት ቀርቦ ማናገር በጣም ከባድ እንደሚሆን ተሰምቶት ሊሆን ይችላል፤ በኋላ ላይ እንደታየው ግን ጲላጦስን ማናገር ያን ያህል ከባድ አልነበረም። ጲላጦስ የኢየሱስን መሞት የመቶ አለቃውን ጠይቆ ካረጋገጠ በኋላ አስከሬኑን እንዲወስድ ለዮሴፍ ፈቀደለት። በዚህ ጊዜ በኢየሱስ ሞት ሐዘን ክፉኛ የተደቆሰው ዮሴፍ እየተጣደፈ ኢየሱስ ወደተገደለበት ቦታ ተመልሶ ሄደ። —ማር. 15:42-45

  • የአርማትያሱ ዮሴፍ ከእውነት ጎን ቆመ
    መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2017 | ጥቅምት
    • የሳንሄድሪን ሸንጎ አባል

      በመንፈስ ቅዱስ መሪነት የተጻፈው የማርቆስ ወንጌል ዮሴፍን “የተከበረ የሸንጎ አባል” በማለት ይጠራዋል። ሸንጎ የሚለው ቃል በዚህ አገባቡ የሚያመለክተው የአይሁድ ከፍተኛ ፍርድ ቤትና ጠቅላይ የአስተዳደር አካል የነበረውን ሳንሄድሪንን እንደሆነ ግልጽ ነው። (ማር. 15:1, 43) በመሆኑም ዮሴፍ ከሕዝቡ መሪዎች መካከል አንዱ ነበር ማለት ነው፤ ሮማዊውን ገዥ ፊት ለፊት ቀርቦ ማነጋገር የቻለው በዚህ ምክንያት ሳይሆን አይቀርም። ከዚህ አንጻር ዮሴፍ ሀብታም የነበረ መሆኑም የሚያስገርም አይደለም።—ማቴ. 27:57

      ክርስቲያን መሆንህን ለሌሎች በይፋ የመናገር ድፍረት አለህ?

      የሳንሄድሪን ሸንጎ አባላት በቡድን ደረጃ ለኢየሱስ ጥላቻ ነበራቸው። እነዚህ ሰዎች ኢየሱስን ለማስገደል ሴራ ጠንስሰው ነበር። በአንጻሩ ግን ዮሴፍ “ጥሩና ጻድቅ ሰው” ተብሎ ተጠርቷል። (ሉቃስ 23:50) ዮሴፍ ከአብዛኞቹ የሳንሄድሪን ሸንጎ አባላት በተለየ ሐቀኛና ጥሩ ሥነ ምግባር የነበረው ሰው ከመሆኑም ሌላ የአምላክን ትእዛዛት ለመጠበቅ የተቻለውን ያህል ጥረት ያደርግ ነበር። በተጨማሪም ይህ ሰው “የአምላክን መንግሥት ይጠባበቅ [እንደነበር]” ተገልጿል፤ የኢየሱስ ደቀ መዝሙር የሆነውም በዚህ ምክንያት ሳይሆን አይቀርም። (ማር. 15:43፤ ማቴ. 27:57) የኢየሱስን መልእክት እንዲቀበል ያነሳሳው ለእውነትና ለፍትሕ ያለው ልባዊ ፍላጎት ሊሆን ይችላል።

  • የአርማትያሱ ዮሴፍ ከእውነት ጎን ቆመ
    መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2017 | ጥቅምት
    • ፍርሃቱን አሸነፈ

      ኢየሱስ በሞተበት ወቅት ዮሴፍ ፍርሃቱን አሸንፎና ከኢየሱስ ተከታዮች ጎን ለመቆም ወስኖ እንደነበር ከሁኔታዎች መረዳት ይቻላል። ማርቆስ 15:43 ላይ የሚገኘው ሐሳብ ይህን በግልጽ ያሳያል፤ ጥቅሱ “ደፍሮም ወደ ጲላጦስ ገባና የኢየሱስ አስከሬን እንዲሰጠው ጠየቀ” ይላል።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ