-
መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ወረርሽኝ ምን ይላል?የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
-
-
መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ወረርሽኝ አስቀድሞ ተናግሯል?
መጽሐፍ ቅዱስ እንደ ኮቪድ-19፣ ኤድስ ወይም የኅዳር በሽታ ያሉ ወረርሽኞችን በስም ጠቅሶ ትንቢት አይናገርም። ሆኖም “ቸነፈር” እና “ገዳይ መቅሰፍት” እንደሚከሰት አስቀድሞ ተናግሯል። (ሉቃስ 21:11፤ ራእይ 6:8) እነዚህ ክንውኖች ‘የመጨረሻዎቹ ቀናት’ ወይም “የዚህ ሥርዓት መደምደሚያ ምልክት” ገጽታዎች ናቸው።—2 ጢሞቴዎስ 3:1፤ ማቴዎስ 24:3
-
-
መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ወረርሽኝ ምን ይላል?የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
-
-
ሉቃስ 21:11፦ “ቸነፈር ይሆናል።”
የሚያስተላልፈው መልእክት፦ በስፋት የተሰራጩ የጤና ችግሮች የመጨረሻዎቹ ቀናት ምልክት ገጽታዎች ናቸው።
-