የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ከበሽታ የጸዳ ዓለም
    ንቁ!—2004 | ሰኔ 8
    • የአምላክ መንግሥት መቼ ይመጣል ብለን መጠበቅ እንችላለን? ኢየሱስ ለዚህ ጥያቄ መልስ ሲሰጥ የአምላክ መንግሥት እርምጃ ሊወስድ መቃረቡን የሚያመለክቱ ተከታታይ ክስተቶች እንደሚኖሩ ተንብዮአል። ከእነዚህ ምልክቶች አንዱ ምን እንደሆነ ሲገልጽ “ቸነፈር በተለያየ ስፍራ ይከሠታል” ብሏል። (ሉቃስ 21:10, 11፤ ማቴዎስ 24:3, 7) “ቸነፈር” ተብሎ የተተረጎመው የግሪክኛ ቃል “ማንኛውንም ለሞት የሚያደርስ ተላላፊ በሽታ” ያመለክታል። በ20ኛው መቶ ዘመን በሕክምና ሳይንስ ረገድ ከፍተኛ የሆነ እድገት ቢታይም በጣም አስከፊ የሆኑ ቸነፈሮች ተከስተዋል።—“ከ1914 ወዲህ በተከሰቱ ቸነፈሮች የሞቱ ሰዎች” የሚለውን ሣጥን ተመልከት።

      ኢየሱስ በወንጌሎች ውስጥ ከተናገረው ቃል ጋር የሚመሳሰለው የራእይ መጽሐፍ ትንቢት ኢየሱስ ክርስቶስ በሰማይ ሥልጣኑን በሚይዝበት ጊዜ አጅበው የሚከተሉት ፈረሰኞች እንደሚኖሩ ይገልጻል። አራተኛው ፈረሰኛ ‘በግራጫ ፈረስ’ ላይ ተቀምጦ “መቅሠፍት” እያስከተለ ያልፍ ነበር። (ራእይ 6:2, 4, 5, 8) ከ1914 ወዲህ በተከሰቱት ዋና ዋና ተላላፊ በሽታዎች ምክንያት የሞቱት ሰዎች ብዛት በእርግጥም ይህ ምሳሌያዊ ፈረሰኛ በመጋለብ ላይ መሆኑን ያረጋግጥልናል። በዚህ “መቅሠፍት” ሳቢያ በመላው ዓለም የደረሰው መከራ የአምላክ መንግሥት የሚመጣበት ጊዜ በጣም ቅርብ ለመሆኑ ተጨማሪ ማረጋገጫ ይሰጠናል።b—ማርቆስ 13:29

  • ከበሽታ የጸዳ ዓለም
    ንቁ!—2004 | ሰኔ 8
    • [በገጽ 12 ላይ የሚገኝ ሣጥን]

      ከ1914 ወዲህ በተከሰቱ ቸነፈሮች የሞቱ ሰዎች

      እነዚህ አሐዛዊ መረጃዎች ግምታዊ ናቸው። ቢሆንም የሰው ልጅ ከ1914 ወዲህ በቸነፈሮች ምን ያህል እንደተጠቃ ያሳያሉ።

      ◼ ፈንጣጣ (ከ300 ሚሊዮን እስከ 500 ሚሊዮን) ለፈንጣጣ አስተማማኝ የሆነ መድኃኒት አልተገኘም። ዓለም አቀፋዊ በሆነ የክትባት ፕሮግራም አማካኝነት በመጨረሻ በ1980 ሊወገድ ችሏል።

      ◼ ሳንባ ነቀርሳ (ከ100 ሚሊዮን እስከ 150 ሚሊዮን) በአሁኑ ጊዜ ሳንባ ነቀርሳ በግምት በየዓመቱ ሁለት ሚሊዮን ገደማ የሚሆኑ ሰዎችን ይገድላል። በተጨማሪም በምድር ላይ ከሚኖሩ 3 ሰዎች መካከል አንዱ በደሙ ውስጥ የሳንባ ነቀርሳ ባክቴሪያ ይገኝበታል።

      ◼ ወባ (ከ80 ሚሊዮን እስከ 120 ሚሊዮን) በ20ኛው መቶ ዘመን የመጀመሪያ አጋማሽ በየዓመቱ በወባ የሚሞቱ ሰዎች ብዛት ሁለት ሚሊዮን ያህል ነበር። በአሁኑ ጊዜ ሰዎች በብዛት በወባ የሚሞቱት ከሰሐራ በታች ባሉ የአፍሪካ አገሮች ውስጥ ሲሆን አሁንም በየዓመቱ ከአንድ ሚሊዮን የሚበልጡ ሰዎችን ይገድላል።

      ◼ የኅዳር በሽታ (ከ20 ሚሊዮን እስከ 30 ሚሊዮን) አንዳንድ ታሪክ ጸሐፊዎች በዚህ በሽታ ያለቁት ሰዎች ቁጥር ከዚህ በእጅጉ እንደሚበልጥ ይናገራሉ። ይህ ቀሳፊ በሽታ የመጣው የመጀመሪያውን ዓለም ጦርነት እግር ተከትሎ ሲሆን በ1918 እና 1919 መላውን ምድር አዳርሷል። ማን ኤንድ ማይክሮብስ የተባለው መጽሐፍ “ቡቦኒክ ቸነፈር እንኳን ይህን በሚያክል ፍጥነት ይህን የሚያክሉ ሰዎችን አልገደለም” ይላል።

      ◼ ተስቦ (20 ሚሊዮን ገደማ) አብዛኛውን ጊዜ ጦርነት ሲነሳ የተስቦ ወረርሽኝ አብሮ ይከሰታል። አንደኛው የዓለም ጦርነትም የምሥራቅ አውሮፓ አገሮችን ያጨደ የተስቦ ወረርሽኝ እንዲነሳ ምክንያት ሆኗል።

      ◼ ኤድስ (ከ20 ሚሊዮን በላይ) ይህ ዘመናዊ መቅሠፍት በየዓመቱ ሦስት ሚሊዮን የሚያክሉ ሰዎችን ይገድላል። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የኤድስ ፕሮግራም በሰጠው ግምታዊ አሐዝ መሠረት “በሽታውን ለመከላከልና ለማከም ከፍተኛ ጥረት ካልተደረገ . . . ከ2000 እስከ 2020 ባሉት ዓመታት 68 ሚሊዮን ሰዎች ይሞታሉ።”

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ