የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w12 10/1 ገጽ 15
  • ይህን ያውቁ ኖሯል?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ይህን ያውቁ ኖሯል?
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2012
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የአንባቢያን ጥያቄዎች
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2003
  • ‘ከይሖዋ ቀን’ በሕይወት የሚተርፈው ማን ነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1997
  • የይሖዋ የእሳት ፈረሶችና የጦር ሠረገሎች
    ከመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች ምን ትማራለህ?
  • የራስን ጥቅም የመሰዋትና በታማኝነት የመጣበቅ ምሳሌ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1997
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2012
w12 10/1 ገጽ 15

ይህን ያውቁ ኖሯል?

ኢየሩሳሌም በ70 ዓ.ም. ከመጥፋቷ በፊት ክርስቲያኖች ከይሁዳ ሸሽተው እንደወጡ የሚያሳይ ማስረጃ አለ?

የሮም ሠራዊት የጥንቷን ኢየሩሳሌም ሲያጠፋ

“ኢየሩሳሌም በጦር ሠራዊት ተከባ ስታዩ መጥፊያዋ እንደቀረበ እወቁ። በዚህ ጊዜ በይሁዳ ያሉ ወደ ተራሮች ይሽሹ፤ በከተማይቱ ውስጥ ያሉም ከዚያ ይውጡ።” (ሉቃስ 21:20, 21) ኢየሱስ በኢየሩሳሌም ላይ የሚመጣውን ጥፋት አስመልክቶ ለደቀ መዛሙርቱ ከላይ ያለውን መመሪያ ሰጥቶ ነበር። ታዲያ ደቀ መዛሙርቱ ኢየሱስ የሰጠውን ማስጠንቀቂያ ሰምተው እርምጃ እንደወሰዱ የሚያሳይ ማስረጃ አለ?

ኢየሱስ ከሞተ ከበርካታ አሥርተ ዓመታት በኋላ በሴስቲየስ ጋለስ የሚመራው የሮም ሠራዊት በአካባቢው የተነሳውን ዓመፅ ለማስቆም ወደ ፓለስቲና መጣ። በወቅቱ ይኖር የነበረው ጆሴፈስ የተባለው አይሁዳዊ የታሪክ ምሁር ይህ ወረራ እንደተካሄደ አረጋግጧል። የሮም ሠራዊት ኢየሩሳሌምን የከበበ ሲሆን በወቅቱ ከተማይቱን ድል የሚያደርጋት ይመስል ነበር። ይሁን እንጂ ጋለስ ሠራዊቱ ወደ ኋላ እንዲያፈገፍግ በድንገት ትእዛዝ ሰጠ። ዩሲቢየስ የተባለው የአብያተ ክርስቲያናት ታሪክ ጸሐፊ እንደገለጸው በይሁዳ የነበሩት ክርስቲያኖች ይህን አጋጣሚ ተጠቅመው በዲካፖሊስ ተራራማ አካባቢ ወደምትገኘው ፔላ የተባለች ከተማ ሸሹ።

ከጥቂት ዓመታት በኋላ ማለትም በ70 ዓ.ም. በጄኔራል ቲቶ የሚመራ ሌላ የሮም ሠራዊት የአይሁድ ዋና ከተማ የሆነችውን ኢየሩሳሌምን ከበባት። በዚህ ጊዜ የመጣው የሮም ሠራዊት፣ በጋለስ የሚመራው ሠራዊት ሳይፈጽም የተመለሰውን ነገር ማከናወን ይኸውም ኢየሩሳሌምን መደምሰስ ችሏል። ከከተማዋ መውጣት ያልቻሉ በመቶ ሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል።

‘የነቢያት ልጆች’ የተባሉት እነማን ናቸው?

የሳሙኤልን፣ የኤልያስን እና የኤልሳዕን ታሪኮች በሚገልጹት የመጽሐፍ ቅዱስ ዘገባዎች ላይ ‘የነቢያት ማኅበር’ ወይም ‘የነቢያት ልጆች’ (የ1954 ትርጉም) ተብለው ስለተጠቀሱ ወንዶች እናነባለን። ለምሳሌ ያህል፣ ኤልሳዕ “ከነቢያት ማኅበር [“ልጆች፣”የ1954 ትርጉም] አንዱን ጠርቶ” ኢዩን የእስራኤል ንጉሥ አድርጎ እንዲቀባው ልኮታል።—2 ነገሥት 9:1-4

‘የነቢያት ልጆች’ የሚለው ስም የሚያመለክተው ቃል በቃል የነቢያትን ልጆች ሳይሆን አንድ ላይ የሚማሩ ወይም አንድ ላይ የሚኖሩና የሚሠሩ ሰዎች የፈጠሩትን ማኅበር እንደሆነ ምሁራን ይናገራሉ። ጆርናል ኦቭ ቢብሊካል ሊትሬቸር እንደሚገልጸው የዚህ ማኅበር አባላት “መንፈሳዊ አባት በሆናቸው ነቢይ ሥር ሆነው ያህዌን [ይሖዋን] ለማገልገል ራሳቸውን ሙሉ በሙሉ ያቀረቡ ሰዎች” ሳይሆኑ አይቀሩም። (2 ነገሥት 2:12) እንዲያውም ኢዩ ንጉሥ ሆኖ መቀባቱን በሚገልጸው የመጽሐፍ ቅዱስ ዘገባ ላይ ኤልሳዕ የላከው ሰው “የነቢዩ አገልጋይ” ተብሎ ተጠርቷል።—2 ነገሥት 9:4 NW

‘የነቢያት ልጆች’ ቀላል ሕይወት ይመሩ የነበረ ይመስላል። በኤልሳዕ ዘመን የነበረው ማኅበር አባላት ለራሳቸው መኖሪያ እንደሠሩና ይህን ሥራ ለማከናወን መጥረቢያ ተውሰው እንደነበረ ተገልጿል። (2 ነገሥት 6:1-5) “የነቢያት ማኅበር ወገን” የነበረ ባሏን በሞት ያጣች ሴት በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ መጠቀሷ ከመካከላቸው አንዳንዶቹ አግብተው እንደነበር ይጠቁማል። (2 ነገሥት 4:1) ታማኝ እስራኤላውያን የነቢያቱ ልጆች ለሚያከናውኑት ሥራ አድናቆት የነበራቸው ይመስላል፤ እንዲያውም አንድ እስራኤላዊ ምግብ ይዞላቸው እንደመጣ የሚናገር የመጽሐፍ ቅዱስ ዘገባ አለ።—2 ነገሥት 4:38, 42

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ