-
ተስፋ የተሰጠበት ልጅኢየሱስ—መንገድ፣ እውነት፣ ሕይወት
-
-
ይህ ከሆነ በኋላ ከአንድ ወር የሚበልጥ ጊዜ አለፈ፤ ኢየሱስም 40 ቀን ሞላው። ታዲያ በዚህ ጊዜ ወላጆቹ ወዴት ይወስዱታል? ካረፉበት ቦታ በስተ ሰሜን ጥቂት ኪሎ ሜትሮች ርቀት ላይ ወደሚገኘው በኢየሩሳሌም ወዳለው ቤተ መቅደስ ወሰዱት። በሕጉ መሠረት ወንድ ልጅ ከተወለደ ከ40 ቀናት በኋላ እናትየዋ ወደ ቤተ መቅደሱ ሄዳ የመንጻት መሥዋዕት ማቅረብ ይኖርባታል።—ዘሌዋውያን 12:4-8
ማርያምም ያደረገችው ይህንኑ ነው። ለመሥዋዕት ይዛ የመጣችው ሁለት ትናንሽ ወፎችን ነው። ይህም የዮሴፍንና የማርያምን የኑሮ ደረጃ ይጠቁማል። ሕጉ እንደሚያዝዘው ለመሥዋዕት መቅረብ ያለበት የበግ ጠቦትና አንድ ወፍ ነው። ሆኖም እናቲቱ የበግ ጠቦት ለማቅረብ አቅሟ የማይፈቅድላት ከሆነ ሁለት ዋኖሶች ወይም ሁለት የርግብ ጫጩቶች ማቅረብ ትችላለች። ማርያምም አቅሟ የፈቀደላትና ያቀረበችው ይህንን ነው።
-