-
ማርያም ከተወችው ምሳሌ ምን ልንማር እንችላለን?መጠበቂያ ግንብ—2009 | ጥር 1
-
-
ዮሴፍና ማርያም በአንጻራዊ ሁኔታ ሲታይ ድሆች እንደነበሩ መጽሐፍ ቅዱስ ይጠቁማል። ይህን እንዴት እናውቃለን? የማቴዎስ፣ የማርቆስ፣ የሉቃስና የዮሐንስ ወንጌሎች ማርያምንና ዮሴፍን አስመልክተው ከሚናገሯቸው ጥቂት ታሪኮች መካከል፣ ማርያም ከወለደች ከ40 ቀን በኋላ ከዮሴፍ ጋር ወደ ቤተ መቅደሱ ሄደው የሚፈለግባቸውን መሥዋዕት ይኸውም “ሁለት ዋኖሶች ወይም ሁለት የርግብ ጫጩቶች” ማቅረባቸውን የሚገልጸው ሐሳብ ይገኝበታል።a (ሉቃስ 2:22-24) ይህን መሥዋዕት ያቀርቡ የነበሩት የበግ ጠቦት ለማቅረብ አቅም ያልነበራቸው ድሃ ሰዎች ነበሩ። ዮሴፍና ማርያም የዕለት ጉርሳቸውን ለማግኘት ብዙ መድከም ነበረባቸው። ያም ሆኖ ቤታቸው ፍቅር የሰፈነበት ነበር። ለመንፈሳዊ ነገሮች ቅድሚያ ይሰጡ እንደነበር ጥርጥር የለውም።—ዘዳግም 6:6, 7
-
-
ማርያም ከተወችው ምሳሌ ምን ልንማር እንችላለን?መጠበቂያ ግንብ—2009 | ጥር 1
-
-
a ከሁለቱ ወፎች አንዱ የኃጢአት መሥዋዕት ሆኖ የቀረበ ነው። (ዘሌዋውያን 12:6, 8) ማርያም ይህን መሥዋዕት ማቅረቧ እንደ ማንኛውም ሰው እሷም የመጀመሪያው ሰው አዳም የሠራው ኃጢአት ያስከተላቸውን ውጤቶች በሙሉ መውረሷን አምና እንደተቀበለች ያሳያል።—ሮም 5:12
-