የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • የጌታ እራት ለአንተ ትልቅ ትርጉም አለው
    መጠበቂያ ግንብ—2003 | ሚያዝያ 1
    • በተመሳሳይም ወይኑ ምሳሌያዊ ነበር። ኢየሱስ እንዲህ ብሏል:- “ይህ ጽዋ ስለ እናንተ በሚፈሰው በደሜ የሚሆን አዲስ ኪዳን ነው።”​—⁠ሉቃስ 22:20

      በማቴዎስ ዘገባ መሠረት ኢየሱስ ጽዋውን አንስቶ “ስለ ብዙዎች ለኃጢአት ይቅርታ የሚፈስ የአዲስ ኪዳን ደሜ ይህ ነው” በማለት ተናግሯል። (ማቴዎስ 26:28) ኢየሱስ በጽዋው ውስጥ ያለውን ወይን በምሳሌያዊ ሁኔታ ደሙን ለማመልከት ተጠቅሞበታል። የፈሰሰው ደሙ ከእርሱ ጋር በሰማይ ነገሥታትና ካህናት ሆነው የሚገዙት በመንፈስ የተቀቡት ደቀ መዛሙርት ‘በአዲስ ቃል ኪዳን’ ውስጥ እንዲታቀፉ መሠረት ጥሏል።​—⁠ኤርምያስ 31:31-33፤ ዮሐንስ 14:2, 3፤ 2 ቆሮንቶስ 5:5፤ ራእይ 1:4-6፤ 5:9, 10፤ 20:4, 6

      ከዚህም በላይ በጽዋው ውስጥ ያለው ወይን የፈሰሰው የኢየሱስ ደም “ለኃጢአት ይቅርታ” እንደሚያስገኝ ለማስታወስ የሚያገለግል ሲሆን ይህም ከወይኑ የሚካፈሉት ሰዎች ከክርስቶስ ጋር በሰማይ ተባባሪ ወራሾች እንዲሆኑ መንገድ ጠርጎላቸዋል። በመሆኑም በመታሰቢያው በዓል ላይ ከቂጣውና ከወይኑ የሚካፈሉት ሰማያዊ ጥሪ ያላቸው የተወሰኑ ሰዎች ብቻ ናቸው።​—⁠ሉቃስ 12:32፤ ኤፌሶን 1:13, 14፤ ዕብራውያን 9:22፤ 1 ጴጥሮስ 1:3, 4

      በአዲሱ ቃል ኪዳን ውስጥ የማይካተቱት ሌሎቹ የኢየሱስ ተከታዮችስ ተስፋቸው ምንድን ነው? እነዚህ የጌታ “ሌሎች በጎች” ተስፋቸው ከክርስቶስ ጋር በሰማይ መግዛት ሳይሆን ገነት በሆነች ምድር ላይ ለዘላለም መኖር ነው። (ዮሐንስ 10:16፤ ሉቃስ 23:43፤ ራእይ 21:3, 4) ‘አምላክን ሌሊትና ቀን በመቅደሱ የሚያመልኩትና’ “እጅግ ብዙ ሰዎች” የተባሉት እነዚህ ታማኝ ክርስቲያኖች በጌታ እራት በዓል ላይ ተገኝተው በዓሉ ሲከበር የመመልከት መብት በማግኘታቸው ደስተኞች ናቸው። በቃላቸውና በድርጊታቸው “በዙፋኑ ላይ ለተቀመጠው ለአምላካችንና ለበጉ ማዳን ነው” ብለው የሚናገሩ ያህል ነው።​—⁠ራእይ 7:9, 10, 14, 15

  • የጌታ እራት ለአንተ ትልቅ ትርጉም አለው
    መጠበቂያ ግንብ—2003 | ሚያዝያ 1
    • [በገጽ 5, 6 ላይ የሚገኝ ሣጥን/ሥዕል]

      “ይህ ሥጋዬ ነው” ወይስ “ይህ ማለት ሥጋዬ ነው”?

      ኢየሱስ “እኔ የበጎች በር ነኝ” ወይም “እውነተኛ የወይን ግንድ እኔ ነኝ” ብሎ ሲናገር ቃል በቃል በር ወይም የወይን ግንድ ነው ብለን አናስብም። (ዮሐንስ 10:7፤ 15:1) በተመሳሳይም መጽሐፍ ቅዱስ “ይህ ጽዋ . . . አዲስ ኪዳን ነው” ሲል ጽዋው ራሱ ቃል በቃል አዲስ ኪዳን እንደሆነ አድርገን አናስብም። ልክ እንደዚያው ሁሉ ኢየሱስ ቂጣው ሥጋው ‘እንደሆነ’ ሲናገር ቂጣው ሥጋውን እንደሚያመለክት መናገሩ እንደሆነ ምንም ጥርጥር የለውም። በመሆኑም በቻርልስ ቢ ዊሊያምስ የተዘጋጀው መጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሱን “ይህ ሥጋዬን ያመለክታል” በማለት ተርጉሞታል።​—⁠ሉቃስ 22:19, 20

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ