-
የአንባቢያን ጥያቄዎችመጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2018 | ኅዳር
-
-
ኢየሱስ ከመሞቱ በፊት በነበረው ምሽት ሐዋርያቱን በእምነት ባልንጀሮቻቸው መካከል የክብር ቦታ ለማግኘት መጣጣር እንደሌለባቸው መክሯቸዋል። እንዲህ ብሏቸዋል፦ “የአሕዛብ ነገሥታት በእነሱ ላይ ሥልጣናቸውን ያሳያሉ፤ እንዲሁም በሕዝባቸው ላይ ሥልጣን ያላቸው ሰዎች በጎ አድራጊዎች ተብለው ይጠራሉ። እናንተ ግን እንዲህ አትሁኑ።”—ሉቃስ 22:25, 26
-
-
የአንባቢያን ጥያቄዎችመጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2018 | ኅዳር
-
-
ታዲያ ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ “እናንተ ግን እንዲህ አትሁኑ” ሲላቸው ምን ማለቱ ነበር? ለማኅበረሰቡ ችግር ደንታ ቢሶች እንዲሆኑ ማለትም በዙሪያቸው ስላለው ሕዝብ ደህንነት እንዳያስቡ እየነገራቸው ነበር? በጭራሽ። ኢየሱስን ያሳሰበው የልግስና ድርጊት ለመፈጸም የሚነሳሱበት ዓላማ መሆን አለበት።
በኢየሱስ ዘመን የነበሩ ባለጸጋ ሰዎች በስፖርት ውድድር ቦታዎች ለሚቀርቡ ትርኢቶችና ጨዋታዎች የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ፣ መናፈሻዎችንና ቤተ መቅደሶችን በመገንባት እንዲሁም እንዲህ ያሉ ሌሎች እንቅስቃሴዎችን በመደገፍ ጥሩ ስም ለማትረፍ ይሞክሩ ነበር። ሆኖም ዓላማቸው አድናቆትና ተወዳጅነት ማትረፍ ወይም በምርጫ ወቅት ብዙ ሰው እንዲመርጣቸው ማድረግ ነበር። አንድ የማመሣከሪያ ጽሑፍ “ከእነዚህ ሰዎች መካከል ከልባቸው ተነሳስተው ልግስና የሚያሳዩ ሰዎች ቢኖሩም የአብዛኞቹ ዓላማ ግን ፖለቲካዊ ጥቅም ማግኘት ነበር” በማለት ይገልጻል። ኢየሱስ ተከታዮቹን ያሳሰባቸው እንዲህ ያለውን ከፍ ያለ ቦታ ላይ የመድረስ ፍላጎትና የግል ጥቅምን የማራመድ ዝንባሌ እንዲያስወግዱ ነበር።
ከተወሰኑ ዓመታት በኋላ ሐዋርያው ጳውሎስ፣ ለመስጠት የምንነሳሳበትን ትክክለኛ ዓላማ አስመልክቶ ሲጽፍ ይህን አስፈላጊ እውነት ጎላ አድርጎ ገልጿል። በቆሮንቶስ ለነበሩ የእምነት ባልንጀሮቹ “አምላክ በደስታ የሚሰጠውን ሰው ስለሚወድ እያንዳንዱ ሰው ቅር እያለው ወይም ተገዶ ሳይሆን በልቡ ያሰበውን ይስጥ” በማለት ጽፎላቸዋል።—2 ቆሮ. 9:7
-