የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ጥምቀት ምንድን ነው?
    የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
    • በመንፈስ ቅዱስ መጠመቅ። መጥምቁ ዮሐንስም ሆነ ኢየሱስ ክርስቶስ በመንፈስ ቅዱስ ስለመጠመቅ ተናግረዋል። (ማቴዎስ 3:11፤ ሉቃስ 3:16፤ የሐዋርያት ሥራ 1:1-5) ይህ ጥምቀት በመንፈስ ቅዱስ ስም ከመጠመቅ ጋር አንድ አይደለም። (ማቴዎስ 28:19) እንዲህ የምንለው ለምንድን ነው?

      በመንፈስ ቅዱስ የሚጠመቁት ከኢየሱስ ተከታዮች መካከል የተወሰኑት ብቻ ናቸው። እነዚህ ሰዎች ከክርስቶስ ጋር ነገሥታትና ካህናት ሆነው በምድር ላይ እንዲገዙ ስለተጠሩ በመንፈስ ቅዱስ ይቀባሉ።f (1 ጴጥሮስ 1:3, 4፤ ራእይ 5:9, 10) ገነት በምትሆነው ምድር ላይ ለዘላለም የመኖር ተስፋ ያላቸው በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ የኢየሱስ ተከታዮች ተገዢዎቻቸው ይሆናሉ።—ማቴዎስ 5:5፤ ሉቃስ 23:43

  • ጥምቀት ምንድን ነው?
    የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
    • በእሳት መጠመቅ። መጥምቁ ዮሐንስ እያዳመጡት ለነበሩት ሰዎች እንዲህ ብሏቸዋል፦ “እሱ [ኢየሱስ] በመንፈስ ቅዱስና በእሳት ያጠምቃችኋል። ላይዳውን በእጁ ይዟል፤ አውድማውንም ፈጽሞ ያጸዳል፤ ስንዴውንም ወደ ጎተራ ያስገባል፤ ገለባውን ግን በማይጠፋ እሳት ያቃጥለዋል።” (ማቴዎስ 3:11, 12) በእሳት በመጠመቅና በመንፈስ ቅዱስ በመጠመቅ መካከል ልዩነት እንዳለ ልብ በል። ዮሐንስ ይህን አገላለጽ የተጠቀመው ምንን ለማመልከት ነው?

      ስንዴው የሚያመለክተው ኢየሱስን ሰምተው የሚታዘዙትን ሰዎች ነው። እነዚህ ሰዎች በመንፈስ ቅዱስ የመጠመቅ ተስፋ አላቸው። ገለባው፣ ኢየሱስን ለመስማት ፈቃደኛ ያልሆኑ ሰዎችን ያመለክታል። የእነዚህ ሰዎች መጨረሻ በእሳት መጠመቅ ነው፤ ይህም ዘላለማዊ ጥፋትን ያመለክታል።—ማቴዎስ 3:7-12፤ ሉቃስ 3:16, 17

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ