-
ኢየሱስ የአምላክ ጽድቅ ጎልቶ እንዲታይ ያደረገው እንዴት ነው?መጠበቂያ ግንብ—2010 | ነሐሴ 15
-
-
7. ኢየሱስ ምን ውድ ነገሮች ነበሩት?
7 ኢየሱስ ለአምልኮ በሚደረጉ ስብሰባዎች ላይ አዘውትሮ በመገኘት ለመንፈሳዊ ነገሮች ከፍተኛ ጉጉት እንዳለው አሳይቷል። ፍጹም አእምሮ ስለነበረው ከዕብራይስጥ ቅዱሳን መጻሕፍት ሲነበብ የሰማውንም ሆነ ያነበበውን ነገር ሁሉ በደንብ ተረድቶት ነበር። (ሉቃስ 4:16) ኢየሱስ ውድ የሆነ ሌላም ነገር ይኸውም ለሰው ልጆች መሥዋዕት አድርጎ ሊያቀርበው የሚችለው ፍጹም ሰብዓዊ አካል ነበረው። በተጠመቀበት ወቅት እየጸለየ የነበረ ሲሆን በመዝሙር 40:6-8 ላይ በሚገኘው ትንቢታዊ ሐሳብ ላይ አሰላስሎ ሊሆን ይችላል።—ሉቃስ 3:21፤ ዕብራውያን 10:5-10ን አንብብ።a
-
-
ኢየሱስ የአምላክ ጽድቅ ጎልቶ እንዲታይ ያደረገው እንዴት ነው?መጠበቂያ ግንብ—2010 | ነሐሴ 15
-
-
a ሐዋርያው ጳውሎስ ከመዝሙር 40:6-8 ላይ ሲጠቅስ የተጠቀመው የግሪክኛውን የሰብዓ ሊቃናት ትርጉም ሲሆን እዚያ ላይ ጥቅሱ “አካል አዘጋጀህልኝ” ይላል። አሁን ባሉ የጥንቶቹ የዕብራይስጥ ቅዱሳን መጻሕፍት ቅጂዎች ላይ ይህ ሐሳብ አይገኝም።
-