የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • jy ምዕ. 21 ገጽ 56-ገጽ 57 አን. 6
  • በናዝሬት በሚገኘው ምኩራብ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • በናዝሬት በሚገኘው ምኩራብ
  • ኢየሱስ—መንገድ፣ እውነት፣ ሕይወት
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ኢየሱስ ባደገባት ከተማ ውስጥ በሚገኝ ምኩራብ
    እስከ ዛሬ ከኖሩት ሁሉ የሚበልጠው ታላቅ ሰው
  • ተአምራት ቢፈጽምም በናዝሬት እንኳ ተቀባይነት አላገኘም
    ኢየሱስ—መንገድ፣ እውነት፣ ሕይወት
  • ከኢያኢሮስ ቤት ወጥቶ እንደገና ወደ ናዝሬት ተጓዘ
    እስከ ዛሬ ከኖሩት ሁሉ የሚበልጠው ታላቅ ሰው
  • ምኩራቦች—ኢየሱስና ደቀ መዛሙርቱ የሰበኩባቸው ቦታዎች
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2010
ለተጨማሪ መረጃ
ኢየሱስ—መንገድ፣ እውነት፣ ሕይወት
jy ምዕ. 21 ገጽ 56-ገጽ 57 አን. 6
ኢየሱስ በምኩራብ ውስጥ ቆሞ ከኢሳይያስ ጥቅልል ላይ ሲያነብ

ምዕራፍ 21

በናዝሬት በሚገኘው ምኩራብ

ሉቃስ 4:16-31

  • ኢየሱስ ከኢሳይያስ ጥቅልል አነበበ

  • የናዝሬት ሰዎች ኢየሱስን ለመግደል ሞከሩ

የናዝሬት ሕዝብ በአድናቆት ተውጧል። ኢየሱስ ከአንድ ዓመት ገደማ በፊት በዮሐንስ ለመጠመቅ ከናዝሬት እስከወጣበት ጊዜ ድረስ የሚታወቀው በአናጺነቱ ነበር። አሁን ግን ተአምር የመፈጸም ችሎታ እንዳለው በስፋት እየተወራ ነው። የከተማዋ ነዋሪዎች በመካከላቸው አንዳንድ ተአምራት ሲሠራ ለመመልከት ጓጉተዋል።

ኢየሱስ እንደ ልማዱ በከተማዋ ውስጥ ወደሚገኘው ምኩራብ ሲሄድ ጉጉታቸው ይበልጥ ጨመረ። በዚያ የሚከናወነው የአምልኮ ሥርዓት ጸሎትን እንዲሁም “በሰንበት ቀናት ሁሉ በምኩራቦች” እንደሚደረገው ከሙሴ መጻሕፍት ማንበብን ይጨምራል። (የሐዋርያት ሥራ 15:21) ከዚህም ሌላ ከነቢያት መጻሕፍት የተወሰኑ ክፍሎች ይነበባሉ። ኢየሱስ ለማንበብ ሲነሳ፣ ወደዚያ ምኩራብ ይመጣ በነበረባቸው ዓመታት የሚያውቃቸውን ብዙ ሰዎች ሳይመለከት አልቀረም። እዚያም የነቢዩ ኢሳይያስን ጥቅልል ሰጡት። እሱም በይሖዋ መንፈስ ስለተቀባው ሰው የሚናገረውን ቦታ አወጣ፤ ይህ ጥቅስ በዛሬው ጊዜ በኢሳይያስ 61:1, 2 ላይ ይገኛል።

ኢየሱስ፣ አስቀድሞ የተነገረለት ይህ ሰው ለተማረኩት ነፃነትና ለታወሩት ማየትን እንዲሁም የይሖዋ ሞገስ የሚገኝበትን ቀን መቅረብ እንደሚያውጅ የሚገልጸውን ሐሳብ አነበበ። ከዚያም ጥቅልሉን ለአገልጋዩ መልሶ ሰጠውና ተቀመጠ። ሁሉም ትኩር ብለው እየተመለከቱት ነው። ኢየሱስ በዚህ ወቅት ረዘም ላለ ጊዜ ሳይናገር አልቀረም፤ ከተናገረው መካከል “ይህ አሁን የሰማችሁት የቅዱሳን መጻሕፍት ቃል ዛሬ ተፈጸመ” የሚለው ትልቅ ትርጉም ያለው ሐሳብ ይገኝበታል።—ሉቃስ 4:21

ሰዎቹ “ከአፉ በሚወጡት የሚማርኩ ቃላት” ተደነቁ፤ እርስ በርሳቸውም “ይህ የዮሴፍ ልጅ አይደለም እንዴ?” ይባባሉ ጀመር። ሆኖም ኢየሱስ እንደፈጸመ የሰሟቸውን ዓይነት ተአምራት ሲያከናውን ለመመልከት ፈልገዋል፤ እሱም ይህን ስለተገነዘበ እንዲህ አለ፦ “‘አንተ ሐኪም፣ እስቲ ራስህን አድን’ የሚለውን አባባል እንደምትጠቅሱብኝ ጥርጥር የለውም። ‘በቅፍርናሆም እንደተደረገ የሰማነውን ነገር እዚህ በራስህ አገርም አድርግ’ ትሉኛላችሁ።” (ሉቃስ 4:22, 23) የኢየሱስ የቀድሞ ጎረቤቶች፣ ኢየሱስ ለአገሩ ሰዎች ቅድሚያ ሊሰጥ ስለሚገባ ሰዎችን መፈወስ መጀመር ያለበት ከአካባቢው እንደሆነ ተሰምቷቸው ሊሆን ይችላል። በመሆኑም ኢየሱስ የናቃቸው መስሏቸው ይሆናል።

ኢየሱስ አስተሳሰባቸው ስለገባው በእስራኤል ታሪክ ውስጥ የተፈጸሙ አንዳንድ ክንውኖችን ጠቀሰ። በኤልያስ ዘመን በእስራኤል ውስጥ ብዙ መበለቶች ቢኖሩም ኤልያስ ግን ከእነዚህ ወደ አንዳቸውም እንዳልተላከ ገለጸ። ኤልያስ የሄደው በሲዶና አቅራቢያ በምትገኝ ሰራፕታ በተባለች ከተማ ወደምትኖር እስራኤላዊት ያልሆነች መበለት ነው፤ በዚያ የፈጸመው ተአምርም የሴትየዋንና የልጇን ሕይወት አትርፏል። (1 ነገሥት 17:8-16) በኤልሳዕ ዘመንም በእስራኤል ብዙ የሥጋ ደዌ ሕመምተኞች ነበሩ፤ ሆኖም ነቢዩ ያነጻው ሶርያዊውን ንዕማንን ብቻ ነው።—2 ነገሥት 5:1, 8-14

ምኩራቡ ውስጥ የነበሩት ሰዎች ኢየሱስን ከተራራው አናት ላይ ሊወረውሩት ሲወስዱት

ኢየሱስ ባደገበት ከተማ የነበሩት ሰዎች፣ ራስ ወዳድነታቸውንና እምነተ ቢስነታቸውን ለማጋለጥ ኢየሱስ እንዲህ ያለ ንጽጽር መጠቀሙ ተገቢ እንዳልሆነ ተሰምቷቸው ይሆናል፤ በዚህ ጊዜ ምን አደረጉ? በምኩራቡ የነበሩት ሰዎች እጅግ ስለተቆጡ ተነስተው ኢየሱስን እያጣደፉ ከከተማው አስወጡት። የናዝሬት ከተማ ወደምትገኝበት ተራራ አፋፍ በመውሰድ ቁልቁል ሊወረውሩት ሞከሩ። ሆኖም ኢየሱስ ከእጃቸው አምልጦ በሰላም ሄደ። ከዚያም በገሊላ ባሕር ሰሜናዊ ምዕራብ ዳርቻ ላይ ወደምትገኘው ወደ ቅፍርናሆም ተጓዘ።

  • ኢየሱስ ባደገባት በናዝሬት ሕዝቡ በአድናቆት የተዋጠው ለምንድን ነው?

  • ሰዎቹ የኢየሱስን ንግግር ሲሰሙ ምን ተሰማቸው? ሆኖም ያስቆጣቸው ምንድን ነው?

  • የናዝሬት ሰዎች ኢየሱስን ምን ሊያደርጉት ሞከሩ?

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ