የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • “አዲሲቱ ዓለም ትርጉም”​—ምሁራን እውነተኛ ሆኖ አግኝተውታል
    መጠበቂያ ግንብ—1991 | መጋቢት 1
    • በአዲሲቱ ዓለም ትርጉም መሠረት በሉቃስ 4:18 ላይ ኢየሱስ “የይሖዋ መንፈስ በእኔ ላይ ነው” በማለት የኢሳይያስን ትንቢት ጠቅሶ በእሱ ላይ እንደተፈጸመ ገልጾአል። (ኢሳይያስ 61:1) ብዙዎች እዚህ ላይ ይሖዋ የሚለው ስም መጠቀሱን ይቃወማሉ። ይሁን እንጂ ይህ አዲስ ኪዳን በሚባለው የአዲሲቱ ዓለም ትርጉም የክርስቲያን ግሪክኛ ቅዱሳን ጽሑፎች ውስጥ ያ ስም ከሰፈረባቸው ከ200 ከሚበልጡ ቦታዎች ውስጥ አንዱ ብቻ ነው። እውነት ነው አሁን በእጅ ካሉት የቀድሞ ‘የአዲስ ኪዳን’ የግሪክኛ የእጅ ጽሑፎች ውስጥ በማንኛቸውም ላይ የአምላክ የግል ስም አይገኝም። ይሁን እንጂ ምክንያታዊ ባልሆነ ድንገት ደራሽ ፍላጎት ሳይሆን በጠንካራ ምክንያቶች ስሙ በአዲሲቱ ዓለም ትርጉም ገብቷል። ሌሎችም ተመሳሳይ መንገድ ተከትለዋል። በጀርመንኛ ቋንቋ ብቻ 11 ትርጉሞች “ይሖዋ” የሚለውን ስም ወይም “በአዲስ ኪዳን” ጽሑፎች ውስጥ የዕብራይስጡን “ያህዌህ” ቃል በቃል ትርጉም ሲጠቀሙ ሌሎች አራት ትርጉሞች ግን “ጌታ” ከሚለው (የማዕረግ ስም) በማስከተል በቅንፍ ውስጥ ስሙን ይጨምራሉ።c ከ70 በላይ የጀርመንኛ ትርጉሞች በግርጌ ማስታወሻዎቻቸው ወይም ሐተታዎቻቸው ውስጥ ስሙን ተጠቅመውበታል።

  • “አዲሲቱ ዓለም ትርጉም”​—ምሁራን እውነተኛ ሆኖ አግኝተውታል
    መጠበቂያ ግንብ—1991 | መጋቢት 1
    • c ጆሃን ባቦር፣ ካርል ኤፍ ባርድት፣ ፔትረስ ዶሽ፣ ዊልሄልም ኤም፣ ኤል ዴዌቴ፣ ጆርጅ ኤፍ ጊሪሲንገር፣ ሄይንሪክ ኤ ደብልዩ ሜዬር፣ ፍሬድሪክ ሙንተር፣ ሴባስትያን ማስቼል፣ ጆሃን ሲ ኤፍ እስኩልዝ፣ ጆሃን ጄ እስቶልዝ፣ እና ዶሚኒክስ ቮን ብሬንታኖ፣ ኦገስት ዳሼል፣ ፍሬድሪክ ሃውክ፣ ጆሃን ፒ ላንጅና ሉድዊግ ሬይን ሃርት ስሙን በቅንፍ ይዘዋል።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ