-
ይህን ያውቁ ኖሯል?መጠበቂያ ግንብ—2010 | መጋቢት 1
-
-
ኢየሱስ “ባረጀ አቁማዳ አዲስ የወይን ጠጅ የሚያስቀምጥ ሰው የለም” ብሎ የተናገረው ለምንድን ነው?
▪ በጥንት ጊዜ ከእንስሳት ቆዳ በተሠራ አቁማዳ ውስጥ ወይን ጠጅ ማስቀመጥ የተለመደ ነበር። (ኢያሱ 9:13) አቁማዳ እንደ ግልገል ወይም ፍየል ካሉ የቤት እንስሳት ቆዳ ይሠራ ነበር። አቁማዳ የሚሠራው ፍየሉ ከታረደ በኋላ ጭንቅላቱና እግሮቹ ተቆርጠው ቆዳው ምንም ቦታ ሳይቆረጥ ሙሉውን በመግፈፍ ነው። ከዚያም ቆዳው ይለፋና አንገቱ ወይም አንድ እግር ብቻ ሲቀር ሌሎች ቀዳዳዎች በሙሉ ይሰፋሉ፤ ይህ ያልተሰፋው ክፍል የአቁማዳው አፍ ሆኖ ያገለግላል። የአቁማዳው አፍ በውታፍ ይዘጋል ወይም በሲባጎ ይታሰራል።
ከጊዜ በኋላ ቆዳው ስለሚቆረፍድ እንደልብ ሊለጠጥ አይችልም። በመሆኑም ያረጀ አቁማዳ እየፈላ የሚሄድ አዲስ ወይን ጠጅ ለማስቀመጥ አይሆንም። ምክንያቱም ወይኑ እየፈላ ሲሄድ የቆረፈደውን ቆዳ ሊያፈነዳው ይችላል። በሌላ በኩል አዲስ አቁማዳ የመለጠጥ ባሕርይ ስላለው አዲስ ወይን ሲፈላ የሚኖረውን ግፊት መቋቋም ይችላል። ኢየሱስ ከላይ ያለውን ሲናገር በወቅቱ በሚገባ የሚታወቀውን አንድ ሐቅ እየጠቀሰ ነበር። አንድ ሰው አዲስ የወይን ጠጅ ባረጀ አቁማዳ ውስጥ ቢያስቀምጥ ምን ሊከሰት እንደሚችል ሲገልጽ እንዲህ ብሏል፦ “አዲሱ የወይን ጠጅ አቁማዳውን ያፈነዳዋል፤ የወይን ጠጁም ይፈስሳል፤ አቁማዳውም ከጥቅም ውጭ ይሆናል። ስለዚህ አዲስ የወይን ጠጅ በአዲስ አቁማዳ መጨመር አለበት።”—ሉቃስ 5:37, 38
-
-
ይህን ያውቁ ኖሯል?መጠበቂያ ግንብ—2010 | መጋቢት 1
-
-
[በገጽ 15 ላይ የሚገኝ ሥዕል]
ያረጀ አቁማዳ
-