-
“ጠላቶቻችሁን ውደዱ” ሲባል ምን ማለት ነው?የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
-
-
“የሚረግሟችሁን መርቁ።” (ሉቃስ 6:28) ጠላቶቻችን ክፉ ቃል ቢናገሩንም እነሱን በደግነትና በአሳቢነት በማነጋገር ‘የሚረግሙንን መመረቅ’ እንችላለን። መጽሐፍ ቅዱስ “ስድብን በስድብ አትመልሱ። ከዚህ ይልቅ ባርኩ” ይላል። (1 ጴጥሮስ 3:9) ይህ ምክር የጥላቻን ሰንሰለት ለመበጠስ ይረዳናል።
“ለሚሰድቧችሁ ጸልዩ።” (ሉቃስ 6:28) አንድ ሰው ከሰደባችሁ “በክፉ ፋንታ ክፉ አትመልሱ።” (ሮም 12:17) ከዚህ ይልቅ አምላክ ግለሰቡን ይቅር እንዲለው ጸልዩ። (ሉቃስ 23:34፤ የሐዋርያት ሥራ 7:59, 60) ለመበቀል ከመሞከር ይልቅ አምላክ ፍጹም በሆነው የፍትሕ መሥፈርቱ መሠረት እንዲፈርድበት ጉዳዩን ለእሱ ተዉት።—ዘሌዋውያን 19:18፤ ሮም 12:19
“ጠላቶቻችሁን ውደዱ፤ ለሚጠሏችሁ መልካም አድርጉ፤ የሚረግሟችሁን መርቁ፤ እንዲሁም ለሚሰድቧችሁ ጸልዩ።”—ሉቃስ 6:27, 28
-