የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w10 9/1 ገጽ 15
  • ይህን ያውቁ ኖሯል?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ይህን ያውቁ ኖሯል?
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2010
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ኢየሱስ በቤተሰብ ውስጥ ያሳለፈው የልጅነት ሕይወት
    እስከ ዛሬ ከኖሩት ሁሉ የሚበልጠው ታላቅ ሰው
  • ኢየሱስ ታዛዥነትን ተምሯል
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2010
  • “የነጎድጓድ ልጆች” ተብለው ተጠርተዋል
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2011
  • ስለ ኢየሱስ ቤተሰቦች ምን ያህል ታውቃለህ?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2003
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2010
w10 9/1 ገጽ 15

ይህን ያውቁ ኖሯል?

ከ12ቱ ሐዋርያት መካከል ከኢየሱስ ጋር የሚዛመድ አለ?

▪ ቅዱሳን መጻሕፍት ይህን በተመለከተ ቀጥተኛ መልስ አይሰጡም። ይሁን እንጂ አንዳንድ መረጃዎች እንዲሁም ሲወርዱ ሲዋረዱ የመጡ ታሪኮች እንደሚናገሩት ከሆነ ከ12ቱ ሐዋርያት መካከል የተወሰኑት የኢየሱስ ዘመዶች የነበሩ ይመስላል።

የወንጌል ዘጋቢዎች፣ ኢየሱስ በመከራ እንጨት ላይ ተሰቅሎ በነበረበት ጊዜ ይመለከቱት የነበሩትን ሴቶች ስም ጽፈዋል። ዮሐንስ 19:25 “እናቱ [ማርያም]፣ የእናቱ እህት፣ የቀልዮጳ ሚስት ማርያምና መግደላዊት ማርያም” በማለት የአራቱን ማንነት ይጠቅሳል። ይህን ጥቅስ ማቴዎስና ማርቆስ ሁኔታውን ከገለጹበት መንገድ ጋር ስናነጻጽረው የማርያም እህት የተባለችው ሴት ሰሎሜ ናት ወደሚል መደምደሚያ ሊያደርሰን ይችላል። በተጨማሪም ሰሎሜ የዘብዴዎስ ልጆች እናት ተብላ የተጠራችው ሴት ሳትሆን አትቀርም። (ማቴዎስ 27:55, 56፤ ማርቆስ 15:40) እንዲህ ከሆነ፣ ሌላ ጥቅስ ላይ ልጆቿ እንደሆኑ የተጠቀሱት ያዕቆብና ዮሐንስ የኢየሱስ የአክስት ልጆች ናቸው ማለት ነው። ኢየሱስ ዓሣ አጥማጆች የነበሩትን እነዚህን ወንድማማቾች ደቀ መዛሙርቱ እንዲሆኑ ጥሪ አቅርቦላቸዋል።—ማቴዎስ 4:21, 22

ከመጽሐፍ ቅዱስ ውጭ የሆኑ ሲወርዱ ሲዋረዱ የመጡ ታሪኮች ደግሞ በዮሐንስ 19:25 ላይ ከተጠቀሱት ሴቶች መካከል የአንዷ ባል የሆነው ቀልዮጳ ወይም እልፍዮስ የኢየሱስ አሳዳጊ አባት የሆነው የዮሴፍ ወንድም እንደሆነ ይናገራሉ። እነዚህ ታሪኮች በእውነታ ላይ የተመሠረቱ ከሆነ ከ12ቱ ሐዋርያት አንዱ የሆነውና የእልፍዮስ ልጅ የተባለው ያዕቆብ የኢየሱስ የአጎት ልጅ ይሆናል ማለት ነው።—ማቴዎስ 10:3

ኢየሱስና አጥማቂው ዮሐንስ የሚዛመዱት እንዴት ነው?

▪ የዚህን ጥያቄ መልስ ለማግኘት በመጀመሪያ የዮሐንስ እናት ኤልሳቤጥና የኢየሱስ እናት ማርያም ያላቸውን ዝምድና ማወቅ ይኖርብናል። ሁለቱ ስላላቸው ዝምድና የተለያዩ መላ ምቶች ይሰነዘራሉ። ለምሳሌ ያህል፣ አንዳንዶች ኤልሳቤጥና ማርያም የአንድ አያት ልጆች እንደሆኑ አድርገው ሲናገሩ ሌሎች ደግሞ ኤልሳቤጥ የማርያም አክስት እንደሆነች ይሰማቸዋል።

ሉቃስ 1:36 ላይ ተመዝግቦ እንደምናገኘው መልአኩ ለማርያም “እነሆ፣ ዘመድሽ ኤልሳቤጥም በስተርጅናዋ ወንድ ልጅ ፀንሳለች” ብሏት ነበር። እዚህ ጥቅስ ላይ “ዘመድ” ተብሎ የተተረጎመው ግሪክኛ ቃል የተወሰነን ዝምድና አያመለክትም። ኢንተርፕሪተርስ ዲክሽነሪ ኦቭ ዘ ባይብል የተሰኘው መዝገበ ቃላት እንደገለጸው “ቃሉ ሰፊ ትርጉም ያለው ከመሆኑ የተነሳ እንዴት እንደሚዛመዱ በትክክል ለመለየት አያስችልም።” በተጨማሪም ዘ ካቶሊክ ኢንሳይክሎፒዲያ “ስለ ማርያም ወላጆች . . . ያሉን መረጃዎች በሙሉ . . . ከአዋልድ መጻሕፍት የተገኙ ናቸው” በማለት ይህ ትምህርት ከየት እንደመጣ ገልጿል። እንግዲያው በማርያምና በኤልሳቤጥ መካከል ያለው ዝምድና ምን እንደሆነ በትክክል አይታወቅም፤ በመሆኑም ዮሐንስና ኢየሱስ እንዴት እንደሚዛመዱ እርግጠኞች መሆን አንችልም። ይሁን እንጂ ኢየሱስና ዮሐንስ ቢያንስ ቢያንስ የሩቅ ዝምድና እንዳላቸው ምንም ጥርጥር የለውም።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ