የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • አንድ ሳምራዊ እውነተኛ ባልንጀራ መሆኑን አሳየ
    ኢየሱስ—መንገድ፣ እውነት፣ ሕይወት
    • ኢየሱስ ሰውየውን “በትክክል መልሰሃል፤ ዘወትር ይህን አድርግ፤ ሕይወትም ታገኛለህ” አለው። ይሁንና ውይይቱ በዚህ አላበቃም። ሰውየው የፈለገው ቀጥተኛ መልስ አይደለም፤ ከዚህ ይልቅ “ጻድቅ መሆኑን ለማሳየት” እንዲሁም አመለካከቱ ትክክለኛ እንደሆነና ሌሎችን የሚይዝበት መንገድ ተገቢ መሆኑን ኢየሱስ እንዲያረጋግጥለት ፈልጓል። ስለዚህ “ለመሆኑ ባልንጀራዬ ማን ነው?” የሚል ጥያቄ አቀረበ። (ሉቃስ 10:28, 29) ይህ ቀላል የሚመስል ጥያቄ ጠለቅ ያለ ትርጉም አለው። እንዴት?

      አይሁዳውያን “ባልንጀራ” የሚለው ቃል የሚያመለክተው የአይሁዳውያንን ባሕል የሚጠብቁ ሰዎችን ብቻ እንደሆነ ያምናሉ፤ በዘሌዋውያን 19:18 ላይ ያለው ሐሳብም ይህን የሚደግፍ ሊመስል ይችላል። እንዲያውም አንድ አይሁዳዊ፣ ከሌላ ዘር ጋር ለመቀራረብ “ሕጉ እንደማይፈቅድ” ሊናገር ይችላል። (የሐዋርያት ሥራ 10:28) ስለዚህ ሕግ አዋቂውና ምናልባትም አንዳንድ የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት፣ ለሌሎች አይሁዳውያን ደግነት ካሳዩ ጻድቃን እንደሆኑ አድርገው ራሳቸውን ይቆጥራሉ። ይሁንና አይሁዳዊ ያልሆነን ሰው እንደ “ባልንጀራቸው” ስለማይመለከቱት በደግነት ላይዙት ይችላሉ።

  • አንድ ሳምራዊ እውነተኛ ባልንጀራ መሆኑን አሳየ
    ኢየሱስ—መንገድ፣ እውነት፣ ሕይወት
    • ይህ እንዴት ያለ ውጤታማ የማስተማሪያ ዘዴ ነው! ኢየሱስ፣ አይሁዳዊ ያልሆኑ ሰዎችም ባልንጀሮቹ እንደሆኑ ለሕግ አዋቂው በቀጥታ ቢነግረው ኖሮ እሱም ሆነ ውይይቱን የሚያዳምጡ ሌሎች አይሁዳውያን ትምህርቱን ይቀበሉ ነበር? ላይቀበሉ ይችላሉ። ይሁን እንጂ ኢየሱስ፣ አድማጮቹ በሚያውቁት ሁኔታ ላይ የተመሠረተና ለመረዳት የማይከብድ ታሪክ መናገሩ “ለመሆኑ ባልንጀራዬ ማን ነው?” የሚለው ጥያቄ መልስ ቁልጭ ብሎ እንዲታይ አድርጓል። እውነተኛ ባልንጀራ የሆነው፣ ቅዱሳን መጻሕፍት በሚያዙት መሠረት ፍቅርና ደግነት ያሳየው ሰው ነው።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ