የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • አንድ ሳምራዊ መልካም ባልንጀራ ሆኖ ተገኘ
    መጠበቂያ ግንብ—1998 | ሐምሌ 1
    • ከዚህ ሁኔታ አንፃር ኢየሱስ የአይሁድን ሕግ ጠንቅቆ ያውቅ ለነበረ ሰው የተናገራቸው ቃላት ከፍተኛ ትምህርት ያዘሉ ነበሩ። ሰውየው ወደ ኢየሱስ ቀረበና እንዲህ ሲል ጠየቀው:- “መምህር ሆይ፣ የዘላለምን ሕይወት እንድወርስ ምን ላድርግ?” ኢየሱስ ጥያቄውን ሲመልስ ‘ጌታ አምላክህን በፍጹም ልብህ በፍጹም ነፍስህም በፍጹም ኃይልህም በፍጹም አሳብህም ውደድ’ እና ‘ባልንጀራህንም እንደ ራስህ ውደድ’ በማለት ወደሚያዘው የሙሴ ሕግ ላይ እንዲያተኩር አደረገ። ከዚህ በመቀጠል ሕግ አዋቂው “ባልንጀራዬስ ማን ነው?” ሲል ኢየሱስን ጠየቀው። (ሉቃስ 10:​25-29፤ ዘሌዋውያን 19:​18፤ ዘዳግም 6:​5) እንደ ፈሪሳውያን አባባል ከሆነ “ባልንጀራ” የሚለው ቃል የሚያገለግለው የአይሁዳውያንን ወግ ለሚጠብቁ ብቻ እንጂ ለአሕዛብና ለሳምራውያን አልነበረም። ይህ የሕግ አዋቂ ኢየሱስ ይህንን አመለካከት ይደግፋል ብሎ አስቦ ከነበረ ጨርሶ ያልጠበቀው መልስ ሊያገኝ ነው።

  • አንድ ሳምራዊ መልካም ባልንጀራ ሆኖ ተገኘ
    መጠበቂያ ግንብ—1998 | ሐምሌ 1
    • ለእኛ የሚሆን ትምህርት

      ለኢየሱስ ጥያቄ ያቀረበለት ሰው ጥረቱ ‘ራሱን ለማጽደቅ’ ነበር። (ሉቃስ 10:​29) ምናልባትም የሙሴን ሕግ ጠንቅቆ ስለሚከተል ኢየሱስ ያወድሰኛል ብሎ አስቦ ሊሆን ይችላል። ሆኖም ይህ ተመፃዳቂ ግለሰብ “የሰው መንገድ ሁሉ በዓይኑ ፊት የቀናች ትመስለዋለች፤ እግዚአብሔር ግን ልብን ይመዝናል” የሚለው የመጽሐፍ ቅዱስ ምሳሌ የያዘውን ሐቅ መቀበል አስፈልጎታል።​—⁠ምሳሌ 21:​2

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ