የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ጎረቤትህን መውደድ ያለብህ ለምንድን ነው?
    መጠበቂያ ግንብ—1993 | መስከረም 15
    • ከዚያም ጠያቂው ኢየሱስን “ባልንጀራዬስ [ጎረቤቴስ አዓት] ማን ነው?” ሲል ጠየቀው። ኢየሱስ በቀጥታ ከመመለስ ይልቅ በወንበዴዎች ስለ ተዘረፈ፣ ስለ ተደበደበና በሕይወትና በሞት መካከል ትተውት ስለሄዱ ስለ አንድ አይሁዳዊ ምሳሌያዊ ታሪክ ነገረው። በዚያው መንገድ ላይ ሁለት አይሁዳውያን አለፉ፤ የመጀመሪያው ካህን ሌላው ደግሞ ሌዋዊ ነበር። ሁለቱም እንደ እነርሱ አይሁዳዊ የነበረው ሰው የደረሰበትን ሁኔታ አስተውለዋል። ነገር ግን እርሱን ለመርዳት ምንም አላደረጉም። ቀጥሎ አንድ ሳምራዊ መጣ። እርሱም አዘነለትና የተጎዳውን አይሁዳዊ ቁሰሎች በጨርቅ አሠራቸው፤ ከዚያም ወደ እንግዶች ማረፊያ ወሰደውና ለሚደረግለት ተጨማሪ እንክብካቤ የሚያስፈልገውን ወጪ ከፍሎለት ሄደ።

      ኢየሱስ ጠያቂውን “እንግዲህ ከነዚህ ከሦስቱ በወንበዴዎች እጅ ለወደቀው ባልንጀራ [ጐረቤት አዓት] የሆነው ማንኛው ይመስልሃል?” አለው። ርኅሩኁ ሳምራዊ እንደነበረ ግልጽ ነው። እውነተኛ የጎረቤት ፍቅር የጎሳ ልዩነት የማያግደው መሆኑን ኢየሱስ በዚህ መንገድ አሳይቷል። — ሉቃስ 10:​29–37

  • የጎረቤት ፍቅር ማሣየት ይቻላል
    መጠበቂያ ግንብ—1993 | መስከረም 15
    • የኢየሱስ መልካም ምሳሌ

      በመጀመሪያው መቶ ዘመን የነበሩት አይሁዳውያን በይሁዳና በገሊላ መካከል ለሚኖሩት ሳምራውያን ጠንካራ የጥላቻ ስሜት ነበራቸው። በአንድ ወቅት አይሁዳውያን ተቃዋሚዎች ኢየሱስን በንቀት “ሳምራዊ እንደ ሆንህ ጋኔንም እንዳለብህ በማለታችን መልካም እንል የለምን?” ሲሉ ጠየቁት። (ዮሐንስ 8:​48) አንዳንድ አይሁድ ለሳምራውያን የነበራቸው የጥላቻ ስሜት በጣም የከረረ ከመሆኑ የተነሳ በምኩራቦቻቸው እንኳ ሳይቀር በግልጽ ይረግሟቸውና ሳምራውያንን የዘላለም ሕይወት እንዳይሰጣቸው በየዕለቱ ይጸልዩ ነበር።

      ኢየሱስ በወንበዴዎች የተደበደበውን አይሁዳዊ ሰው በመንከባከብ እውነተኛ ጎረቤት መሆኑን ስላስመሰከረው ሳምራዊ ሰው ምሳሌ እንዲሰጥ የገፋፋው በአይሁዶች ውስጥ የተተከለውን የጥላቻ ስሜት ማወቁ እንደሆነ አያጠራጥርም። የሙሴን ሕግ ጠንቅቆ ያውቅ የነበረው ሰው “ባልንጀራዬስ [ጎረቤቴስ አዓት] ማን ነው?” ብሎ ሲጠይቀው ኢየሱስ ምን ብሎ ሊመልስለት ይችል ነበር? (ሉቃስ 10:​29) ኢየሱስ በቀጥታ ‘ጎረቤትህ ማለት መሰል አይሁዳዊ ብቻ ሳይሆን ሌሎችንም ሰዎች እንዲያውም ሳምራውያንንም ጭምር ያጠቃልላል’ ብሎ ሊመልስለት ይችል ነበር። ይሁን እንጂ አይሁዳውያን ይህን ለመቀበል አስቸጋሪ ይሆንባቸው ነበር። ስለዚህ ከአንድ ሳምራዊ ምሕረትን ስላገኘ አይሁዳዊ የሚገልጽ ምሳሌ ተናገረ። በዚህ መንገድ ኢየሱስ አይሁዳውያን አድማጮቹን የእውነተኛ ጎረቤት ፍቅር አይሁዳውያን ያልሆኑትንም ይጨምራል ወደሚል መደምደሚያ እንዲደርሱ ረዳቸው።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ