የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ይህን ያውቁ ኖሯል?
    መጠበቂያ ግንብ—2010 | ጥር 1
    • በ⁠ሉቃስ 1:63 ላይ የተገለጸው የመጻፊያ ጽላት ምን ዓይነት ነበር?

      ▪ የሉቃስ ወንጌል እንደዘገበው ዘካርያስን የተወለደው ወንድ ልጁ ማን ተብሎ እንዲጠራ እንደሚፈልግ ወዳጆቹ ጠይቀውት ነበር። በዚህ ጊዜ ዘካርያስ “የእንጨት ጽላት እንዲያመጡለት ጠየቀና ‘ስሙ ዮሐንስ ነው’ ብሎ ጻፈ።” (ሉቃስ 1:63) አንድ የጽሑፍ ሥራ እዚህ ላይ “ጽላት” ተብሎ የተተረጎመው የግሪክኛ ቃል “ብዙውን ጊዜ ከእንጨት ተሠርቶ ሰም በመቀባት የሚዘጋጅ አነስተኛ የመጻፊያ ጽላት” እንደሚያመለክት ገልጿል። እርስ በርስ በተያያዙ የእንጨት ጣውላዎች ላይ ያለው ሰርጎድ ያለው ስፍራ ሰም ይቀባል። ከዚያም አንድ ጸሐፊ ሹል በሆነ መጻፊያ አማካኝነት በዚህ ጣውላ ላይ ማስታወሻ መጻፍ ይችል ነበር። ከዚያም በላዩ ላይ የተጻፈውን ማስታወሻ አጥፍቶ ጽላቱን እንደገና በማለሰስለስ ጥቅም ላይ እንዲውል ማድረግ ይቻላል።

      ማንበብና መጻፍ በኢየሱስ ዘመን የሚለው መጽሐፍ እንዲህ ይላል፦ “በፖምፔ የሚዘጋጁ ሥዕሎች፣ በሮም የተለያዩ ግዛቶች የሚሠሩ ቅርጻ ቅርጾች እንዲሁም ከግብፅ እስከ ሃድርያን ግንብ [ሰሜን ብሪታንያ] ድረስ በሚገኙ በርካታ ቦታዎች ላይ ተቆፍረው የወጡ ሕያው ምሳሌዎች፣ ጽላቶች በስፋት ጥቅም ላይ ይውሉ እንደነበር ያመለክታሉ።” እንዲህ ያሉ ጽላቶች ከተለያዩ ግለሰቦች ለምሳሌ ከነጋዴዎች፣ ከመንግሥት ባለሥልጣናት ምናልባትም በመጀመሪያው መቶ ዘመን ከነበሩ አንዳንድ ክርስቲያኖች እጅ አይጠፉም ነበር።

  • ይህን ያውቁ ኖሯል?
    መጠበቂያ ግንብ—2010 | ጥር 1
    • [በገጽ 11 ላይ የሚገኝ ሥዕል]

      የአንድ ተማሪ ሰም የተቀባ ጽላት፣ ሁለተኛው መቶ ዘመን ዓ.ም.

      [ምንጭ]

      By permission of the British Library

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ