የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • jy ምዕ. 3 ገጽ 14-ገጽ 15 አን. 2
  • መንገድ የሚያዘጋጅ ሰው ተወለደ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • መንገድ የሚያዘጋጅ ሰው ተወለደ
  • ኢየሱስ—መንገድ፣ እውነት፣ ሕይወት
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • መንገድ ጠራጊው ተወለደ
    እስከ ዛሬ ከኖሩት ሁሉ የሚበልጠው ታላቅ ሰው
  • ኤልሳቤጥ ልጅ ወለደች
    ከመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች ምን ትማራለህ?
  • ያለ ነቀፋ በመመላለሳቸው ተክሰዋል
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1994
  • የአንባብያን ጥያቄዎች
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1995
ለተጨማሪ መረጃ
ኢየሱስ—መንገድ፣ እውነት፣ ሕይወት
jy ምዕ. 3 ገጽ 14-ገጽ 15 አን. 2
ማርያም ወደ ቤት ስትገባ ኤልሳቤጥ በሆዷ ያለው ሕፃን በደስታ ሲዘል ተሰማት

ምዕራፍ 3

መንገድ የሚያዘጋጅ ሰው ተወለደ

ሉቃስ 1:57-79

  • መጥምቁ ዮሐንስ ተወለደ፤ እንዲሁም ስም ወጣለት

  • ዮሐንስ ወደፊት ምን እንደሚያከናውን ዘካርያስ ተናገረ

ኤልሳቤጥ የምትወልድበት ጊዜ ደርሷል። ዘመዷ የሆነችው ማርያም ላለፉት ሦስት ወራት እሷ ጋ ቆይታለች። አሁን ግን ማርያም፣ ኤልሳቤጥን ተሰናብታ በስተ ሰሜን በናዝሬት ወደሚገኘው መኖሪያዋ ለመመለስ ረጅሙን ጉዞ የምትያያዝበት ጊዜ ደርሷል። ከስድስት ወር ገደማ በኋላ እሷም ወንድ ልጅ ትወልዳለች።

ማርያም ከሄደች ብዙም ሳይቆይ ኤልሳቤጥ ወለደች። ኤልሳቤጥ በሰላም መገላገሏና እሷም ሆነች ሕፃኑ በጥሩ ጤንነት ላይ የሚገኙ መሆናቸው ምንኛ የሚያስደስት ነው! የኤልሳቤጥ ጎረቤቶችና ዘመዶች ሕፃኑን ሲያዩ ተደሰቱ።

አምላክ ለእስራኤላውያን በሰጠው ሕግ መሠረት ወንድ ልጅ በተወለደ በስምንተኛው ቀን መገረዝ ነበረበት፤ ስም የሚወጣለትም በዚህ ጊዜ ነው። (ዘሌዋውያን 12:2, 3) አንዳንዶች፣ ልጁ ልክ እንደ አባቱ ዘካርያስ ተብሎ እንዲጠራ ሐሳብ አቀረቡ። ሆኖም ኤልሳቤጥ “አይሆንም! ዮሐንስ ይባል” አለች። (ሉቃስ 1:60) መልአኩ ገብርኤል፣ ልጁ ዮሐንስ መባል እንዳለበት መናገሩን አስታውስ።

ጎረቤቶቻቸውና ዘመዶቻቸው ግን “ከዘመዶችሽ መካከል በዚህ ስም የተጠራ ማንም የለም” ሲሉ ተቃወሙ። (ሉቃስ 1:61) ከዚያም ዘካርያስን ልጁ ማን ተብሎ እንዲጠራ እንደሚፈልግ በምልክት ጠየቁት። ዘካርያስ የእንጨት ጽላት እንዲሰጡት ጠየቀና “ስሙ ዮሐንስ ነው” ብሎ ጻፈ።—ሉቃስ 1:63

ዘካርያስ ጽላት ላይ ሲጽፍ፤ ዘካርያስ የመናገር ችሎታው ተመልሶለት ትንቢት ሲናገር

በዚህ ጊዜ የዘካርያስ የመናገር ችሎታ በተአምራዊ መንገድ ተመለሰለት። ዘካርያስ የመናገር ችሎታውን ያጣው፣ ኤልሳቤጥ ልጅ እንደምትወልድ መልአኩ ሲነግረው ባለማመኑ ምክንያት እንደሆነ ታስታውስ ይሆናል። በመሆኑም ዘካርያስ መናገር ሲጀምር ጎረቤቶቹ ሁሉ ተገርመው “የዚህ ሕፃን መጨረሻ ምን ይሆን?” አሉ። (ሉቃስ 1:66) ለዮሐንስ ስም ከወጣበት መንገድ ጋር በተያያዘ የአምላክ እጅ እንዳለበት ተገንዝበው ነበር።

ከዚያ በኋላ ዘካርያስ በመንፈስ ቅዱስ ተሞልቶ እንዲህ አለ፦ “የእስራኤል አምላክ ይሖዋ ፊቱን ወደ ሕዝቡ ስለመለሰና ሕዝቡን ስላዳነ ውዳሴ ይድረሰው። ደግሞም በአገልጋዩ በዳዊት ቤት የመዳን ቀንድ አስነስቶልናል።” (ሉቃስ 1:68, 69) “የመዳን ቀንድ” ሲል በወቅቱ ገና ስላልተወለደው ስለ ጌታ ኢየሱስ መናገሩ ነው። ዘካርያስ፣ በኢየሱስ አማካኝነት አምላክ ምን እንደሚያደርግ ሲናገር እንዲህ ብሏል፦ “ከጠላቶቻችን እጅ ነፃ ካወጣን በኋላ ለእሱ ያለ ፍርሃት ቅዱስ አገልግሎት የማቅረብ መብት ይሰጠናል፤ ይህም ታማኝ እንድንሆንና በሕይወት ዘመናችን ሁሉ ጽድቅ የሆነውን ነገር እንድናደርግ ነው።”—ሉቃስ 1:74, 75

ዘካርያስ ልጁን በተመለከተ ደግሞ የሚከተለውን ትንቢት ተናገረ፦ “አንተ ሕፃን፣ መንገዱን ለማዘጋጀት ቀድመህ በይሖዋ ፊት ስለምትሄድ የልዑሉ ነቢይ ትባላለህ፤ ለሕዝቡም ኃጢአታቸው ይቅር ተብሎላቸው መዳን እንዲያገኙ የሚያስችላቸውን እውቀት ትሰጣቸዋለህ፤ ይህም የሆነው አምላካችን ከአንጀት ስለራራልን ነው። ከዚህ ርኅራኄም የተነሳ እንደ ንጋት ፀሐይ የሚያበራ ብርሃን ከላይ ይወጣልናል፤ ይኸውም በጨለማና በሞት ጥላ ውስጥ ለተቀመጡት ብርሃን ለመስጠት እንዲሁም እግሮቻችንን በሰላም መንገድ ለመምራት ነው።” (ሉቃስ 1:76-79) ይህ ትንቢት ምንኛ የሚያጽናና ነው!

ይህ በእንዲህ እያለ፣ ገና ያላገባችው ማርያም ናዝሬት ወደሚገኘው መኖሪያዋ ደረሰች። ማርገዟ ሲታወቅ ምን ይደርስባት ይሆን?

  • ዮሐንስ፣ ኢየሱስን ምን ያህል ይበልጠዋል?

  • ዮሐንስ ከተወለደ ስምንት ቀን ሲሆነው ምን ነገሮች ተከናወኑ?

  • አምላክ ለዮሐንስ ምን ተልእኮ ይሰጠዋል?

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ