የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ወደ አምላክ መጸለይ ያለብን እንዴት ነው?
    መጠበቂያ ግንብ—1996 | ሐምሌ 15
    • አንድ ደቀ መዝሙር ጸሎት እንዲያስተምራቸው ኢየሱስን በጠየቀው ጊዜ ኢየሱስ ፈቃደኛ ሆኗል። ሉቃስ 11:2-4 (የ1980 ትርጉም) ላይ ተመዝግቦ እንደሚገኘው እንዲህ በማለት መልስ ሰጥቷል፦ “ስትጸልዩ እንዲህ በሉ አላቸው፦ [‘በሰማይ የምትኖር] አባታችን ሆይ! ስምህ ይቀደስ፣ መንግሥትህ ትምጣ፤ የዕለት እንጀራችንን በየቀኑ ስጠን፤ እኛ የበደሉንን ይቅር እንደምንል፣ በደላችንን ይቅር በልልን፣ ወደ ፈተናም አታግባን።’” ይህ ጸሎት የጌታ ጸሎት በመባል ይታወቃል። ጸሎቱ ብዙ ነገሮችን አካትቷል።

  • ወደ አምላክ መጸለይ ያለብን እንዴት ነው?
    መጠበቂያ ግንብ—1996 | ሐምሌ 15
    • በተጨማሪም የሚያሳስቡንን የግል ጉዳዮች በጸሎታችን ውስጥ መጥቀስ እንደምንችል ኢየሱስ አሳይቷል። እንዲህ አለ፦ “የዕለት እንጀራችንን በየቀኑ ስጠን፤ እኛ የበደሉንን ይቅር እንደምንል፣ በደላችንን ይቅር በልልን፣ ወደ ፈተናም አታግባን።” (ሉቃስ 11:3, 4) የኢየሱስ ቃላት በዕለት ተዕለት ጉዳዮቻችን የአምላክን ፈቃድ መጠየቅ እንደምንችልና የሚያስጨንቀን ወይም የሚረብሸን ማንኛውም ነገር ሲያጋጥመን ወደ ይሖዋ መቅረብ እንደምንችል ያሳያሉ። በዚህ መንገድ አምላክን ዘወትር መለመናችን ሕይወታችን በእርሱ ላይ የተመካ መሆኑን እንድንገነዘብ ይረዳናል። ስለዚህ ይሖዋ በሕይወታችን ውስጥ የሚያሳድረውን በጎ ተጽዕኖ ይበልጥ እያወቅን እንሄዳለን። አምላክ በደላችንን ይቅር እንዲለን በየዕለቱ መጠየቃችንም ቢሆን ጠቃሚ ነው። እንዲህ ስናደርግ ያለብንን ድካም ይበልጥ ከማወቃችንም በተጨማሪ ከሌላው ጊዜ በተሻለ ሁኔታ የሌሎችን ጉድለቶች ችለን እንድናልፍ ይረዳናል። በተለይ የዚህን ዓለም የሥነ ምግባር ዝቅጠት ስንመለከት ኢየሱስ ወደ ፈተና አታግባን ብለን እንድንጸልይ የሰጠን ምክር አስፈላጊ ነው። ከዚህ ጸሎት ጋር በመስማማት ወደ መጥፎ ድርጊት ሊመሩን ከሚችሉ ነገሮችና ሁኔታዎች መራቅ አለብን።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ