የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ኢየሱስ ተወለደ—የትና መቼ?
    ኢየሱስ—መንገድ፣ እውነት፣ ሕይወት
    • የሮም ንጉሠ ነገሥት የሆነው አውግስጦስ ቄሳር እያንዳንዱ ሰው እንዲመዘገብ አዋጅ አወጣ። በመሆኑም ዮሴፍና ማርያም ከኢየሩሳሌም በስተ ደቡብ ወደምትገኘው የዮሴፍ የትውልድ ከተማ ይኸውም ወደ ቤተልሔም መጓዝ አለባቸው።

      ለመመዝገብ ወደ ቤተልሔም ብዙ ሰዎች መጥተዋል። በዚህም ምክንያት ዮሴፍና ማርያም፣ አህዮችና ሌሎች እንስሳት በሚያድሩበት ጋጣ ውስጥ ከማረፍ ሌላ አማራጭ አላገኙም። ኢየሱስ የተወለደው በዚህ ቦታ ነው። ማርያምም በጨርቅ ጠቅልላ ለእንስሳቱ ምግብ በሚሰጥበት ግርግም ውስጥ አስተኛችው።

      አውግስጦስ ቄሳር ሕዝቡ እንዲመዘገብ የሚያዝዝ ሕግ እንዲያወጣ ያደረገው አምላክ መሆን አለበት። እንዲህ የምንለው ለምንድን ነው? ምክንያቱም ይህ አዋጅ መውጣቱ ኢየሱስ በቤተልሔም እንዲወለድ ሁኔታዎችን አመቻችቷል፤ ቤተልሔም የኢየሱስ ቅድመ አያት የሆነው የንጉሥ ዳዊት የትውልድ ከተማ ናት። ተስፋ የተሰጠበት ገዢ በዚህች ከተማ እንደሚወለድ ቅዱሳን መጻሕፍት ከረጅም ዘመናት በፊት ተናግረው ነበር።—ሚክያስ 5:2

  • ኢየሱስ ተወለደ—የትና መቼ?
    ኢየሱስ—መንገድ፣ እውነት፣ ሕይወት
    • በዛሬው ጊዜ ብዙ ሰዎች፣ ኢየሱስ የተወለደው በታኅሣሥ ወር እንደሆነ ያምናሉ። ሆኖም በቤተልሔም ታኅሣሥ የዝናብና የቅዝቃዜ ወቅት ነው። እንዲያውም አልፎ አልፎ አመዳይ ይጥላል። በዚያ ወቅት እረኞች ከመንጎቻቸው ጋር ውጭ አያድሩም። በተጨማሪም የሮም ንጉሠ ነገሥት፣ በወቅቱ በእሱ ላይ ለማመፅ ቋፍ ላይ የነበሩት ሕዝቦች በጣም በሚቀዘቅዘው በዚህ ወቅት ለበርካታ ቀናት ተጉዘው እንዲመዘገቡ ያዝዛል ብሎ ማሰብ የማይመስል ነገር ነው። ከሁኔታው መረዳት እንደሚቻለው ኢየሱስ የተወለደው በጥቅምት ወር ነው።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ