-
ኢየሱስ ሀብትን በተመለከተ ምክር ሰጠኢየሱስ—መንገድ፣ እውነት፣ ሕይወት
-
-
የአምላክን መንግሥት እንዲፈልጉ የታዘዙት እነማን ናቸው? ይህን የሚያደርጉት በአንጻራዊ ሁኔታ ሲታይ አነስተኛ ቁጥር ያላቸው ታማኝ ሰዎች እንደሆኑ ኢየሱስ ገልጿል፤ እነዚህን ሰዎችም “ትንሽ መንጋ” ብሏቸዋል። ቁጥራቸው 144,000 ብቻ እንደሚሆን ከጊዜ በኋላ ታወቀ። እነዚህ ሰዎች ምን ሽልማት ተዘጋጅቶላቸዋል? ኢየሱስ “አባታችሁ መንግሥት ሊሰጣችሁ ወስኗል” የሚል ማረጋገጫ ሰጥቷቸዋል። እነዚህ ሰዎች በምድር ሀብት በማከማቸት ላይ ትኩረት አያደርጉም፤ በምድር የሚገኝን ሀብት ሌቦች ሊሰርቁት ይችላሉ። ልባቸው ያረፈው ከክርስቶስ ጋር በሰማይ ሲገዙ በሚያገኙት “የማያልቅ ውድ ሀብት” ላይ ነው።—ሉቃስ 12:32-34
-
-
ታማኙ መጋቢ፣ ዝግጁ ሆነህ ጠብቅ!ኢየሱስ—መንገድ፣ እውነት፣ ሕይወት
-
-
ኢየሱስ፣ ሰማይ ባለው መንግሥት ውርስ የሚያገኘው “ትንሽ መንጋ” ብቻ እንደሆነ ገልጿል። (ሉቃስ 12:32) ይህ አስደናቂ ሽልማት እንደ ቀላል ነገር ሊታይ አይገባም። እንዲያውም አንድ ሰው የመንግሥቱ ወራሽ መሆን እንዲችል ትክክለኛ ዝንባሌ ማዳበሩ ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ ኢየሱስ ጎላ አድርጎ ተናግሯል።
-